የአርበኞች ግንቦት ፯ እና የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ተባበሩ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ግብሬ

ባለፉት ሜይ 15 እስክ 17 2017 ድረስ የአርበኞች ግንቦት 7 እና የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ተወካዮች ስፋ ያለና የጠለቀ ውይይት በፍራንክፈርት ጀርመን አድርገዋል። ተወካዮቹ ዛሬ ባለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ፤የኢኮኖሚ፤ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ህወሃት መሩ የኢህአዴግ መንግስት በአንባገነንነት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈጸመ ስላለው ወንጀል ተነጋግረውበታ።

ተወካዮቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ ዛሬ ያለው የአገራችን ሁኔታ በቶሎ ካልተለወጠ እጅግ ወደ ክፋ የሰአዊና የፖለቲካ ጥፋት ሊደረስ መቻሉ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል። ጥፋቱም ኦጋዴንንም የሚያጠቃልል እንደሚሆን ሁለቱም ወገኖች አምነውበታል።

ተወካዮቹ ያለውን ሁኔት በጥሞና ካሰሉ በኋላ በጋራ ተግባራዊ በመሆን የጋራ ተግባር ለማቀላጠፍ የሚያመቹ ሁኔታዎችን ፈጥሮ በህወሃት\ኢህዴግ አገዛዝ ስር የኢትዮጵያ ህዝብ መማቀቁን እናስቆማለን ብለው መቁረጣቸውን በመግለጫቸው አስፍረዋል።

ሁለቱም ድርጅቶች በሁሉም መንገድ ገዢውን መንግስት አውግዘዋል። የጭቆና የበደል ተግባሩን እንዲያቆምም አስታውቀዋል።

ተወካዮቹ ሌሎችም የትግል ሃይሎች ልክ እንደነሱ በአንድ የጋራ መድረክ ሆነው የህወሃት\ኢህዴግ አገዛዝን አሸንፈው መሸጋገሪያ ዴሞክራሲያዊ ስረአት ለመፍጠር በጋራ በመሆን  እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ሁለቱም ድርጅቶች የዓለማቀፉን ህበረተሰብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆም በገዢው መንግስት ስር የረጅም ጊዜ ስቃዩንና በደሉን እዩለት ብለዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያን የጦር ሰራዊት፤ፖሊስ እና ጸጥታ ሀይሎች የገዛ ህዝባችሁን እየጭቆናችሁ  ህገወጥ አምባገነን መግስትን አትደግፉ ከህዝብ ጋር ወግኑ። ዘላቂ ፍሬ ያለው ለውጥ ባገራቹ አምጡ ይላል የአርበኞች ግንቦት 7 እና የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር የጋራ መግለጫ።