የወልቃይት የአማራ ማንነት የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ክስ ለሰኔ 29 ቀን 2009 ዓ.ም ተቀጠረ

0

በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ
የወልቃይት የአማራ ማንነት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ማለትም በአቶ መብራቱ ጌታሁን፣አቶ አታላይ ዛፌ፣አቶ አለነ ሻማ፣አቶ ጌታቸው አደመ አና አቶ ነጋ ባንቲሁን ክስ ግንቦት 09 ቀን 2009 ዓ.ም በነበረው ቀጠሮ የዓቃቢ ህግ ምስክሮች ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ለዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም መቀጠሩ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት በትናንትናው ዕለት በአውሮፕላን ከትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ተጓጉዘው እንደሚደርሱ ተገልፆ ለመስማት ቀጠሮ የተሰጠባቸው ሁለት ምስክሮች ቀርበው ተደምጠዋል፡፡

ቀሪ 11 የዓቃቢ ህግ ምስክሮች እየመጡ እንደሆነና ደብረ ብርሃን መድረሳቸው ለችሎቱ ተገልፁዋል፡፡ፍርድ ቤቱም እነዚህን ምስክሮች ለመስማት ለሰኔ 29 እና 30 ቀን 2009 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡