ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ ሲሰራበት ከነበረው EBC በገዛ ፈቃዱ ስራውን ለቀቀ

0

አባይ ሚዲያ
አቢሰሎም ፍሰሃ

እኔና ኢቲቪ/ኢቢሲ ተለያይተናል 
ላለፉት አራት ዓመታት ከኢቢሲ ጋር ደጉንም መልካሙን ግዜ ተካፍያለሁ ከሰሞኑ ከተከሰተው የቴዲ አፍሮ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ግን ከህሊናዬ ጋር እየታገልኩ ልቀጥል አልችልም፡፡

ጉዳዩ እንድን የኪነጥበብ ሰው ማቅረብና ያለመቅረብ ጉዳይ ባቻ አይደለም፡፡ የጋዜጠኝነት ልዕልናንም የሚጋፋ ሆኖ ስላገኘሁትና ብዙዎች መሰዋት የከፈሉለትን ሙያ ክብር ለመስጠትም ጭምር ነው እዚህ ውሳኔ ለይ የደርስኩት፡፡

ያለፉትን ስድስት ቀናት በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሳለፍኩ የማውቀው እኔ ነኝ(ግዜው ሲደርስ እናየዋለን)፡፡

እዚህ ውሳኔ ላይ ስደርስ
-በጋዜጠኘነት ሙያ ውስጥ ላላችሁ
-የጋዜጠኝነትን ትምህርት በየዩኒቨርሲቲዎች ለምትማሩ ተማሪዎችና ለምታስተምሩ መምህራን
-መላው የኢትዮጵያን ህዝብን በህሊናዬ እያሰብኩ ነው፡፡

ለኢቢሲ አጠቃላይ ሰራተኞችና በተለያዩ መንገዶች ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ
ዝርዝር ሂደቱን በቅርቡ እንመለከተዋለን፡፡
ስራ ፍለጋው ተጀምሯል ሲል በፌስ ብኩ አስነብቦናል።