ሰበር መረጃ . .( በልኡል ዓለሜ )

0

    አብዛኛዉን አፋኝና ገዳይ አባላቶቹን ያጣዉና እያጣ የሚገኘዉ ብሐራዊ መረጃ በከፍተኛ ሚስጥር ከሐገር ዉጭ አሰልጥኖ ያስገባቸዉ አራት ስናይፐር አነጣጣሪ ገዳዮች፣ ሁለት ልዩ ኮማንዶ የጠለፋ ክፍል ስምሪቶች፣ ሁለት አይቲ ኢንጂነር መረቦች፣  ሁለት አለም አቀፍ ግራና ቀኝ ክንፍ ማንኛዉም አዉቶሞቢል አሽከርካሪዎች፣ ከድተዉ የደረሱበት እንደማይታወቅ በ2008 መጨረሻ ላይ ያሳወቀዉ የብሐራዊ መረጃ የሰዉ ኃይል እና ግንኙነት ክፍሉ በድጋሚ ባሳለፍነዉ ወር  ሚያዚያ 2009 ላይ አንድ እስናይፐር አነጣጣሪና አንድ አይቲ ኢንጂነር ሰልጣኝ ባልታወቀ አካል መገደላቸዉን ለዉስጥ ክፍል ማሳወቁን ምንጮች ጠቆሙ።

   የ10 አለቃ ዝንዉ ክብረት እና የአይቲ ኢንጂነር የሳይበር ጥቃት ባለሞያዋ  ወ/ሪት ሶስና ኤፍሬም የተባሉ ግለሰቦች ቻይናና ህንድ ተምረዉ የተመለሱ እንደነበሩ የጠቆመዉ ምንጫችን ይህን አይነት ድርጊት በመረጃዉ ቢሮ ዉስጥ የተለመደ ነገር እየሆነ ነዉ ሲል ጠቁሟል።

  በተያያዘ መረጃ በወታደራዊ ደህንነት የተግባር ክንፍ ተዋቅሮ የተላከ  አንባ  (  ANBA OPERATION )  የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ለተግባር ተሰማርቶ  የነበረ ቡድን በጎንደር ሊቦ ከምከም አካባቢ በተደረገ ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት በመመታቱ የተግባር መመሪያዉ ውድቅ ( operation  cancelled )  መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

 ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !