በቦኩሃራም የተጠለፉ 82 ልጃገረዶች ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቀሉ

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

በ2014 እኤአ ቦኩሃራም ተጠልፈው ከተወሰዱ 276 ልጃ ገረዶች 82 ዎቹ መለቀቃቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ታወቀ።

እነዚህ ልጃ ገረዶች በናይጄሪያ ቺቦክ በምትባል ከተማ በቦኩሃራም ሚሊሻዎች ተጥልፈው እንደነበረም ተዘግቧል።

ቤተሰቦቻቸውን እስኪቀላቀሉ ድረስም በዋናዋ ከተማ በአቡጃቢ በጸጥታና ደህንነት አካላት ከፍተኛ ጥበቃና ከለላ ሲደረግላቸውም እንደነበረ ለመረዳት ተችሏል።

ልጃገረዶቹን ለማስለቀቅ የናይጄሪያ መንግስት በቁጥጥር ስር አውሏቸው የነበሩትን 5 የቦኩሃራም ሚሊሻዎችን ከእስር መፍታት ግድ ሆኖበታል።

ከዚህ ሁሉ አመታት በሃላ 82 ልጃገረዶች ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በአቡጃቢ ሲቀላቀሉ ያሳዩት እፎይታና ደስታ አስገራሚም እንደነበረ ተዘግቧል።

ምንም እንኩዋን የናይጄሪያ መንግስት ባደረገው ድርድር 82 ልጃገረዶች ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቢገናኙም ወደ 100 የሚቆጠሩ ልጃገረዶች አሁንም በቦኩሃራም ተጥልፈው በቁጥጥር ስር ላይ ይገኛሉ።