ዶናልድ ትራምፕ ሳኡዲ አረብንና ሌሎች የአረብ አገራትን እየጎበኙ ነው

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ አገር ጉብኝታቸው የዓለምን ሚዲያ የሳበ ነው።

ፋናንሺያል ታይምስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅ የዓለም የንግድና የፖለቲካ ሁኔታዎችን የሚከታተል ጋዜጣ ነው። ፋናንሺያል ታይምስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያደርጋሉ የተባለውን ንግግር ጠቅሶ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሽብረተኛነትን መዋጋት “በክፋት እና በደግነት መካከል” የሚደረግ ትግል በለው ያቀርቡታል ይላል።

ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግር ተቀንጭቦ የወጣው ክፍል እስልምና ላይ ያተኮረ ይሆናል ይላል። ይህ ንግግራቸን የኦባማ አስተዳደር ከኢራን ጋር ካደረገው የኑክሌር መሳሪያ ስምምነት ያየይዘዋል ተብሏል። ኢራን እና ሳኡዲ አረብ በጠላትነት የሚተያዩ ናቸው።

በዚህ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጉብኝት ትናት የአማሪካ ኩባንያዎች ከሳኡዲ አረብ ሪያድ ጋር $110 ቢሊዮን የንግድ ስምምነት አድርገዋል።

በሳኡዲ አረብ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበላቸው መስተንግዶ ሲያዋክባቸው ከነበረው የሩሲያ በአሜሪካ ምርጫ  ጣልቃ መግባት ጉዳይ እፎይታ ሰጥቷቸውል ይላል ፋናሺያል ታይምስ።

ዶናልድ ትራምፕ በ2016 በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት “እስልምና ይጠላናል” እያሉ ለተከታዮቻቸው ሲሰብኩ ነበር። እስላሞችም ወደ አሜሪካ መግባት የለባቸውም እስከ ማለትም ደርሰው ነበር። ተቀንጭቦ የወጣው ንግግራቸው ይህንን አባባል አይደግመውም።

ዶናልድ ትራምፕ ለሳኡዲ አረብ መሪዎች በግልጽ የሰባአዊ መብት ጥሰት አያነሱባቸውም ተብሏል። ይህን ጉዳይ ትቶ “የጅሃድ ቡድኖችን እንዋጋ” ላይ ያተኩራል ይባላል። የንግግርራቸው ክፍል “ተባብረን ጠንካራ ስንሆን ብቻ ነው የሰላም ሀያሎች የጥፋት አላማ ያላቸውን የሚያሸንፉት” የሚል እንዳለበት ታውቋል።

የባህሬኑን ንጉስ ሃማድን ዛሬ እሁድ ዶናልድ ትራምፕ አግኝተው “ግንኙነታችን አይሻክርም” ብለዋቸዋል። ይህን ያሉት የኦባማ አስተዳደር ከባህሬን ጋር ቅሬታ ስለነበረው ነው። የባህሬን መንግስት የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ላይ ከፍ ያለጉዳት ሲያደርስ የዓለም አቀፍ ሰባአዊ መብት ድርጅቶች በጣም ወቅሰው ነበር።

የኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ዶናልድ ትራምፕ “ከምንነጋገርባቸው ነገሮች አንዱ ባጣም ብዙ ድንቅ የሆኑ የጦር መሳሪያዎች ጉዳይ ነው። እነዚህን ድንቅ የሆኑ የጦር መሳሪያዎች አንደ አሜሪካ አድርጎ የሚሰራ የለም።” ብለዋቸዋል።

እነዚህ መሳሪያዎች ደግሞ ሳኡዲን ለመቃወሙ የመን የሚገኙ አማጽያንን መምቻ ጥቅም ላይ ይውላል።

የአረብ ዲፕሎማቶች ፋይናንሲያል ታይስ እንደሚለው ዶናልድ ትራምፕ አዲስ የጸረ ሽብር ውጊያ መንገድን አካባቢው አገራት ጋር እየተለሙ ነው ብለው ያምናሉ። በተለይ አይ ሲስ የተባለው አሸባሪ ላይ ያለውን ትኩረት ያነሳሉ። አይ ሲስ በሶሪያ፤ኢራቅ፤ሊቢያ እና ግብጽ ሀይል አለው። በየአገሩ ተንቀሳቃሽ ቡድኖች አለው።  ዓለም አቀፋዊ እና አሜሪካ የምትመራው ህብረት አይሲስ የነበረውን ቦታ በኢራቅ፤ሊቢያ መቀማት ችሏል። አሁን ደግሞ በሶሪያ እያጣበብው ይገኛል የሚል እምነት አላቸው የአረብ ዲፕሎማቶቹ።

የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ተንታኞች የአሜሪካ ከአረቡ ዓለም ጋር በጥብቅ መወዳጀት ካቻይናና ሌሎች ሃያላን ባካባቢው ካላቸው ጥቅም እያስተያዩ ይመዝኑታል። በእግጥ የጸረ ሽብረተኛ ሃይሎች በሌሎች የአረብ አገራት መዳከም፤መጣበብ በአፍሪካ ቀንድ እንደ አል ሸባብ ያሉ አጥፊ ሃይሎች መዳከም አድርገው ያዩታል። ምን ሲባል ቢቆይ ዞሮ ወደ ንግድ ቀልበስ መባሉ የማይቀር ነው። በጊዜው ያለ ወዳጅ ማን ነውን ማሰብ አድርገው ያዩታል።