በእንግሊዝ ማንችስተር ከተማ በኮንሰርት ላይ በደረሱ ፍንዳታዎች 19 ሰዎች ህይወታቸው ሲይልፍ ወደ 50 መጎዳታቸው ተገለጸ

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

እንግሊዙ ማንችስተር ከተማ በሚገኝ የኮንሰርት ማስተናገጃ በደረሰ ፍንዳታ ወደ 19 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተዘግቧል።

ከ50 በላይ የሚሆኑ ክፉኛ መጎዳታቸውንም የማንችስተር ፓሊስ ከሰጠው መግለጫ መረዳት ተችሏል።

የፍንዳታው መንስኤ በትክክል ይፋ ባይሆንም ከአሸባሪ ጥቃት ጋር ግንኙነት ሳይኖረው እንደማይቀር ተገምቷል።

የሽብር ጥቃት ልዩ የምርመራ ቡድኖችም ወደ አከባቢው በመዝለቅ ምርመራ መጀመራቸውም ተዘግቧል።

በዚሁ የኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ ሁለት ከባባድ ፍንዳታዎችን መስማታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

ፍንዳታዎቹ የተከሰቱበት የማንችስተር የኮንሰርት አዳራሽ በታዳሚዎች እስከ አፍጢሙ ሞልቶ እንደነበረ ተዘግቧል።

ይህ የኮንሰርት ማሳያ እስከ 21 000 ሰዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ተገልጿል።