የኤል ሳልቫዶር የጸጥታ ፖሊስ እንስትዋን የሽፍታ አለቃ በቁጥጥር አዋለ

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ማሪሳ ሌሙስ ወይም በቅጽል ስሟ በስፓኝ ቋንቋ “ላ ፓትሮና” ትሰኛለች። በእንግሊዝኛው ደግሞ  “ዘ ቦስ” ስትባል የአማርኛ ፍችው አለቃ ማለት ነው። እድሜዋ 45 ዓመት ነው።

የጽጥታ ፖሊስ የያዛት ከኤል ሳልቫዶር ዋና ከተማ ጓቲማላ ሲቲ እንደገለጸው ማሪሳ ሌሙስ የተያዘችው ከጓቲማላ እስር ቤት አምልጣ በሄደች ከሁለት ሳምንታት በኋላ ነው። የተያዘችው ምእራብ ኤልሳልቫዶር የአገሪቱ ወሰን ዳርቻ ነው።

“ዘ ቦስ” ወንጀልዋ የቅጥር ነብሰ ገዳይ እና አፋኝ ቡድን መሪነትዋ ነው። በዚህም ወንጀል 94 ዓመታት ተፈርዶባት ነው በእስር የነበረችው። ስትያዝ የጸጉርዋን ቀለም ከጥቁር ወደ ቢጫ አቅልማ ነበር ለመሰወር እንዲማቻት ብሏል የአገሪቱ የአገር ግዛት ሚኒስትር ሁኔታውን ሲያስረዳ። ማሪሳ ሌሙስ ያመለጠችው በልዩ ሁኔታ በወታደር ከሚጠበቅ ወህኒ ቤት ነው።

2015 የረጅም ዓመታት የእስራት ፍርድ የተበየነባት በሽፍታ መሪነትዋ ነው። የርስዋ የሚመራው የወንጀል ቡድን ልዩ አፈናዎችን እና በኮንትራት የሚፍጸሙ ግድያዎችን ያከናውን የነበረ ነው።

በዲሴምበር 13 ቀን, 2013 የርስዋ የወንጀል ቡድን የደቡብ ምስራቅ ሞዩታ ግዛትን ከንቲባ በቦምብ ጥቃት ለማድረስ ሞክሯል። ከንቲባው ሳይጎዱ ቀርተዋ። ሆኖም ለሽፍቶቹ ትልቁ ወንጀል ይህ ነበር።

ማሪሳ ሌሙስ ልክ እንዳመለጠች ብዛት ያላቸው ይጠብቋት የነበሩ ወታደሮች ታሰሩ። ዋናው የወህኒ ዘበኛውም ተባሮ ወዲያው አገር አቀፍ እሷን በቁጥጥር የማዋል ዘመቻ ተከፈተ።

ማሪሳ ሌሙስ ልታመልጥ ስትሞክር የመጀመሪያዋ አይደለም። በሜይ ወር አምና እንዲህ ሞክራ አካባቢዋ ካለ ጫካ እንደተደበቀች ፖሊስ ሊይዛት ችሎ ነበር።

ማሪሳ ሌሙስ ሌላ የሚጠብቃት ፍርድ 2013 የገዛ ባልዋን እንዲገደል ተዕዛዝ ሰጥታለች የሚል ነው።

ለመልካም አላማ ቢሆን ጀግና የሚደርጋት ድፍረት የተቸረች ናት።