ሕወሓት 4ኪሎ የገባበትን ቀን ለማክበር በኮሪያ ኤምባሲ ያደረገው ጥሪ በትንታግ ወጣቶች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው

አባይ ሚዲያ
ናትናኤል ኃይለማርያም

በ26 /05/2017 የሕወሓት ኢምባሲ በአምባሳደሩ በሽፈራዉ ጃርሶ ሕወሓት ወደ 4 ኪሎ ቤተ መንግስት የገባበትን ቀን እንደ ኢትዮጵያ የነፃነት ቀን በማስመሰል በደቡብ ኮሪያ የሚገኙትን አባላቶቹንና የሕወሓት ደጋፊዎች የሆኑትን ሆድ አደሮችን ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ዝግጅቴን ያደምቅልኛል በማለት የአፍሪካ አምባሳደሮችን በመጥራት 26ኛ የሕወሓት የስልጣን ዘመኑን በማስመልከት አብዛኛዉን የኢትዮጵያ ሕዝብ በርሃብ እና በከፍተኛ የኑሮ ዉድነት በሚሰቃይበት  በዚህ ሰዓት ከፍተኛ ወጪ በማዉጣት ደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ዉስጥ በሚገኘው ሎቴ ሆቴል ሲቲ ሆል ስቴሽን በሚገኘዉ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ዉስጥ ለመጨፈር በተዘጋጁበት በሲኦል ነዋሪ በሆኑ ትንታግ ኢትዮጵያዉያኖች ከፍተኛ ተቃዉሞ እንደ ገጠማቸዉ ለማወቅ ተችሏል።

የሕዉሐት ኢምባሲ ለዚህ ዝግጅት ባደርገዉ የሚስጥር ጥሪ ወረቀት ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ዘቅዝቆ እንዳወጣዉ ካሰራጨዉ ወረቀት ማየት ተችሏል።  በዚህ የሚስጥር ወረቀት ሌላዉ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ እንዳይሰማ ለማድረግ እና ዝግጅታቸዉን ማንም ሳይሰማ ያለምንም ተቃዉሞ ለማካሔድ የሞከሩት ሙከራ በደቡብ ኮሪያ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሳይሳካላቸዉ ቀርቷል።

በሽፈራዉ ጃርሶ በተጠራዉ የደቡብ ኮርያ የሎቴ ሆቴል ድግስ ላይ ለመገኘት የተገኙት የአፍሪካ ዲፕሎማቲክ ማሕበረሰቦች የሆቴሉ መግቢያ ላይ ባዩት የተቃዉሞ ሰልፍ በጣም በመሸማቀቅ በድግሱ ላይ ብዙ የመቆየት ፍላጎት እንደሌላቸዉ በሚያሳብቅ ፍጥነት ከሆቴሉ ተመልሰዉ ሲወጡ የታየ ሲሆን ከፊሎቹም ተቃዉሞ ሚያካሒዱትን ሲመለሱ ሶሪ በማለት ሲያልፉ ተስተዉለዋል።

ተቃዉሞዉን ያዘጋጁት እንደገለፁልን አስቀድመዉ የጥሪ ወረቀቱ በአጃቸዉ በመግባቱ መሠረት ባስተላለፉት የተቃዉሞ ጥሪ ምክንያት በኢምባሲዉ በሚያደርገዉ ለረጅም ጊዜ ተሳትፎ ሲያደርጉ የነበሩ የሕዉሐት ደጋፊዎች በዚህ ድግስ ላይ አለመገኘታቸዉ አግራሞት እንደፈጠረባቸዉ ሲገልፁ የሕዉሐት ቀኝ አጅ ሆኖ የሚያገለግለዉ ፓስተር ኤፍሬም ግን በዚሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሚደረገዉ የመከራ ድግስ ላይ መገኘቱን እና ለሥርዓቱ ያለዉን ታማኝነት ማሳየቱን ከስፍራዉ ለማወቅ ተችሏል።