የጠፉት ንብረቶች ዝርዝር.

የአፋልጉኝ ማስታወቂያ
# የጠፉት ንብረቶች ዝርዝር…
1ኛ/ እውነት!
2ኛ/ ጽድቅ!
3ኛ/ ፍትህ!
4ኛ/ ማንነት!
5ኛ/ ፍጹም እምነት!
6ኛ/ ቅንነት!
7ኛ/ መከባበር!
8ኛ/ መደጋገፍ!
9ኛ/ ማስተዋል!
10/ አርቆ አሳቢነት!
11/ ፍቅር!
12/ ትሕትና!
13/ ታማኝነት!
14ኛ/ ትእግሥት
15/ ሙሉ ጤንነት! ሲሆኑ…
# ለእነዚህ የሰው ልጅ ውድ አሴቶች መጥፋት ምክንያቶች ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ደግሞ…
1ኛ/ ራስ ወዳድነት!
2ኛ/ ክፋት!
3ኛ/ ምቀኝነት!
4ኛ/ ግብዝነት!
5ኛ/ ስግብግብነት!
6ኛ/ ትዕቢት!
7ኛ/ አድመኝነት!
8ኛ/ ዘረኝነት!
9ኛ/ አላዋቂነት!
10ኛ/ ስካር!
11ኛ/ቂም በቀል!
12ኛ/ድህነት!
14ኛ/ኃጢያተኝነት! ናቸው ተብሎ ይገመታል!
# የጠፉበት ቦታ ….
ከሰው ልጅ ልብና አእምሮ ውስጥ ሲሆን…
# ፈልጎም ሆነ ባጋጣሚ ያገኛቸው ሁሉ ተግባራዊ ቢያደርጋቸው ወሮታውን በሚገባ የሚከፍሉ መሆኑን እንገልጻለን !!!

#########$$$$$$$##########

ልጄ ሆይ ስማኝ
# ለእናትህ
1. ድምፅህን ከድምጿ በላይ ከፍ አታድርግ፡፡
2. አጉል ክርክር አትከራከራት፡፡
3. እሷ ሣትጨርስ አትናገር ፡፡
4. በሥሟ አትጥራት ፡፡
5. እንቅልፏን ሣትጨርስ አትቀስቅሣት ፡፡
6. ለምክኒያት ካልሆነ በቀር ከፊት ለፊቷ
አትቅደም፡፡
7. ባሪያ ለጌታዉ እንደሚተናነሰው ሁሉ
ተናነስላት ፡፡
8. ጠርታህ ሣትጨርስ ‘ አቤት ’ በላት ፡፡
9. ከቤት ወጥተህ አትዘግይባት ፡፡
10. በእይታህ አታፍጥባት ፡፡
11. በንግግርህ አትጋፈጣት ፡፡
12. በቁጣዋ አትቆጣ ፡፡
13. በንግግሯ አትዘባበት ፡፡
14. መላና ሀሣቧን አታናንቅ ፡፡
15. ሲጨንቃት አማክራት ፡፡
16. ሲቸግራት ቀርበህ እርዳት ፡፡
17. ስትታመም አሣክማት ፡፡
18. ስትታረዝ አልብሣት ፡፡
19. ጉዳይዋን ሁሉ ጉዳዬ በል፡፡
20. እቅድ ሀሣቧን ተካፈል ፡፡
21. የሥጋ ዘመዶቿን ቀጥል ፡፡
22. ወዳጆቿን ውደድላት ፡፡
23. ከእርግማኗ ተጠንቀቅ ፡፡
24. እሷን ከማስከፋት ፈፅሞ እራቅ ፡፡
25. ቀስ ብለህ አስረዳት ፡፡
26. በሚገባት ሁኔታና ቋንቋ ንገራት ፡፡
27. ከምርቃቷ ተሽቀዳደም ፡፡
28. ዓላማህን አትደብቃት ፡፡
29. እሷ ሣትቀመጥ አትቀመጥ
…ይህን ሳታደርግ እሷን ብታጣ ግን ፀፀቱ
ይገልሀል! እናቴ የአንቺን ክፉ ፈጣሪ አያሳየኝ!!