ይሄ ሰው ጠገበ፡ ማሰብ ተሳነው

ወንድሙን ጠቁሞ፡ ከስር ሰደደው።

እረ ተው በሉት፡ ይህን አመለኛ

ምሱ ይሰጠውና፡ አርፎ እንዲተኛ።

ሉሌነት ይሻላል፡ ብሎ ገብቷልና

ለሆዱ የሚሆን፡ ሲስፈሩለት ቁና

ጠግቦ አስመለሰው፡ መሬት ወረደና።

ኳስ ሜዳ ቢወስዱት ፡ ትንሽ ዘና እንዲል

ጨዋታውን ረሳው፡ 11 ቁጥሩን ሲከተል ።

ወዳጄ ምን ይሻላል፡ ይህን ሰው እንድ በሉ

አጉራሽ ሆኖ ቀረ ፡ እነሱ ሲበሉ።

መድሃኒቱ ምን ይሆን፡ ሎሌ ለሆነው ሰው

አንጀቱን ሳይነካው፡ ቶሎ  የሚያሽርው።

አንተ የቁም እስርኛ፡ ጉልበትክን አታፍስ

የት ታደርገው ይሆን፡ ስራቱ ሲፈርስ።

እረ ይበቅሃል፡ የሉሌነት ዘመን

እንደ ወንድሞችህ፡ ይሻላል ሰው መሆን።

እረ አንቺ ሴት ወይዘሮ፡ የሱ ባለቤት

ትኖሪበት ይሆን፡ በዚህ ድንጋይ ቤት ።

አቆልቋይ እናምጣ፡ ሰብሰበን ከሃገር

ባልሽ መርⶏልና፡ በቁሙ ተስካር ።

ቅበሩ ተብለን፡ በግዳጅ ብንወጣ

በቁሙ የሞተው ሰው፡ ትልቅ ቀንድ አውጣ።

አባይ  ሲያገሳ፡ በጸሃዩ አገሬ

ሃይል ከማራያም ነው፡ ብዬ ሳስብ ኖሬ

አሁን ነው የገባኛ፡ እጅግ መሳሳቴ

ውዳቂ መሆኑን፡ የደሳለኝ ፍሬ።

ውዳሴ ለእግዚሓቤር፡ ነበረ ወረቡ

አሁን ሆኖ አረፈው ስብሃት  ገንዘቡ።

መች ትጠግብ ይሆን፡ የአስርኛን  እንጅራ  ቀምቶ መብላቱ

ወይ ያኔ  ጉድህ ነው ፡ አይቀር መፈታቱ።

  27 ግንቦት 2009.