የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በሰሜን ጎንደር እስረኞችን ማስፈታታቸው ታወቀ

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ሲሆን ወደ ሲላሪ ከተማ በመግባት በከተማው ያለውን ልዩ እስር ቤት በማጥቃት በስቃይ ላይ የነበሩ 60 እስረኞችን በማስለቀቅ ወደ ነፃነት ኃይሎች እንዲቀላቀሉ አድርገዋል፡፡

በዘመቻው 3 የህወሃት ወታደሮች ከባድ የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው አመራር ሲሰጥ የነበረው አዛዥ ተገድሏል።

በድምሩ 1 በመግደል 3 በማቁሰል እሰሮኞችን የማስወጣቱ ስራም በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። በወቅቱ በተካሄደው ውጊያ የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች ቦታቸውን ጥለው የሸሹ ሲሆን በአካባቢው የህወሃት የካብኔ አባላትም ወጥተው ጥቃቱን መከላከል ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

የእስር ቤት ጠባቂዎችም ከ20 ደቂቃ መታኮስ በሁዋላ ቦታዉን ጥለው ሊሸሹ ችለዋል። በውጊያው 1 የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋይ ቀላል የመቁሰል አደጋ ከማጋጠሙ ውጪ ሌላ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም ለማወቅ ችለናል ። ታስረው ይሰቃዩ የነበሩ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ ከአርበኞች ጋር እንደሚገኙ ታውቋል።