የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ፈተና የ10ኛ ክፍል አማርኛና የ12ኛ ክፍል “ታሪክ ትምህርት” ፈተና ላይም ስተት እንዳለበት ተነገረ

አባይ ሚዲያ ዜና

በአሰግድ ታመነ

ባለፈው ዓመት ለፈተና ከቀረቡት የአማራ ተማሪዎች 32 በመቶ ብቻ ተዘዋወሩ የተባለውና የችግሩ እውነተኛ ምክንያት እስካሁንም ከጥቂት የህወሃት ሰዎችና የትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች ውጭ የማይታወቀው አይነት ደባ ዘንድሮም ተፈፅሟል የተባለ ነው

በመላው ኢትዮጵያ  የአገር አቀፍ ፈተና የ10ኛ ና የ12ኛ ክፍል ፈተና መሰጠቱ ይታወቃል።

በዚህ አገር አቀፍ ፈተና በአማራ ክልል ብቻ ተለይቶ የተሰጡት የፈተና ወረቀቶች ሆን ተብሎ የኮድ መደበላለቅ እንደነበረባቸው ይህም ተፈታኞቹን ተገቢውን ውጤታቸውን ሊያገኙ አችሉም በሚል ተፈርታል

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ የአማርኛ ትምህርት ፈተና ኮድ ለምሳሌ ከጥያቄው ገፅ የመጀመሪያው 011 ይላል ወደ ውስጥ ገፆችን ስታገላብጣቸው ግን ኮዱ ከላይኛው ገፅ ኮድ 011 ጋር መመሳሰል ሲገባው 013 ነው።

ይህ ማለት ፈተናው ሲታረም በተሳሳተ እና በተዘበራረቀ ኮድ መልስ ሊታረም ነው ማለት ነው።በዚህ ውስጥ እንግዲህ ስንት የአማራ ተማሪ ትክክለኛ የልፋት ውጤቱን ሊያገኝ አይችልም ተብላል።

የ10ኛ ክፍል አማርኛ ብቻ ሳይሆን የ12ኛ ክፍል “ታሪክ ትምህርት” ፈተና ላይም ስተት እንዳለበት ይነገራል።

የ12ኛ ክፍል ታሪክ ፈተና 83፣84፣85 እና 86 ኮዶች አሉት።ከእነዚህ ውስጥ 83 እና 85 ኮድ ያላቸው የፈተና ወረቀቶች ልክ እንደ አማርኛ ሁሉ ተመሳሳይ የኮድ አቀማመጥ ችግር አለባቸው ተብላል።

 

ስለዚህ ባለፈው ዓመት ለፈተና ከቀረቡት የአማራ ተማሪዎች 32 በመቶ ብቻ ተዘዋወሩ የተባለውና የችግሩ እውነተኛ ምክንያት እስካሁንም ከጥቂት የህወሃት ሰዎችና የትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች ውጭ የማይታወቀው አይነት ደባ ዘንድሮም ተፈፅሟል ማለት ነው ሲሉ አስተያየት ሰተዋል አንዳንድ አስተማሪዎች።

እሳረኛውና አለውልህ የሚለው የሌለው አማራ ብአዴን በሚባል የህወሃት ረጅም ዱላ ህዝቡን ከማፈን ውጭ የህዝብ ድምፅ መሆን አልቻለም ያሉት እማኞች ሲጠይቁ ደግሞ ከክልላችሁ ያስቀመጥናላችሁን ጠይቁ እንጅ እየተባሉ ምላሽ ሊያገኙ አልቻሉም ተብላል።

ይህን ተከትሎ ሰኔ 2 /2009 የሃገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ላይ የተፈጠረው ስህተት እርማት ላይ አስፈላጊው ማስተካከያ ይደረጋል ሲል መግለጫ ማውጣቱ ታውቃል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ላይ የተፈጠረው ስህተት እርማት ላይ አስፈላጊው ማስተካከያ ይደረጋል ። የሃገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
በዚህ ፈተና የተወሰኑ የትምህርት አይነቶች ላይ የቅደም ተከተል፤ የዓመተ ምህረትና የሚስጥር ቁጥር ስህተት እንደነበረባቸው ታውቋል፡፡ይሁንና ፈተናው ሲታረም አስፈላጊው ማስተካከያ ስለሚደረግ ተማሪዎች ስጋት እንዳይገባቸው የሃገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡