አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ-የ21ወር እስር ፍርድ በገንዘብ ሊወጣው ይችላል ተባለ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ወንድወሰን ተክሉ
የዓለማችን እውቁ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋችና የታዋቂው ባርሴሎና ክለብ አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ በእስፔን ፍርድ ቤት የተፈረደበትን የ21ወር እስር ፍርድ በገንዘብ ለውጦ መክፈል እንደሚችል የእስፔን ጋዜጦችን ጠቅሶ የዘገበው የቢቢሲ ዜና አስታውቃል።

ሜሲ በ2016 ከአባቱ ጋር በታክስና ቀረጥ ማጭበርበር ክስ እያንዳንዳቸው የ21 ወር እስር ፍርድ የተፈረደባቸው ሲሆን አባትዪው ግን በሃላ ላይ መክፈል የሚገባቸውን ታክስ በመክፈላቸው የእስር ግዜያቸው ዝቅ እንዲል መደረጉን ቢቢሲ ዘግባል።

በእስፔን ህግ መሰረት ማንኛውም ከ2ዓመት በታች የእስር ቅጣት የተፈረደበት ፍረደኛ በቀን 400ዩሮ ክፍያ- የሁለት ዓመቱን እስር ወደ ገንዘብ ለውጦ መክፈል እንደሚችል የሚፈቅድ በመሆኑ አሁን ሜሲ ለተፈረደበት የ21 ወር እስር ቅጣት የ$285.000 ዶላር [255.000 ዩሮ] በመክፈል ከእስር መገላገል እንደሚችል የእስፔን ጋዜጦች እየዘገቡ መሆናቸውን የጠቀሰው የቢቢሲ ሪፖርት ይገልጻል።

ሆኖም ይህንን የመጨረሻ የፍቃድ ውሳኔ መስጠት የሚችለው ፍርድ ቤቱ እንደሆነ ታውቃል።

ሌዮኔል ሜሲ ከአባቱ ጆርጅ ጋር ሆኖ ከ2007 እስከ 2009 ባለው ግዜ ውስጥ ከ4.1ሚሊዮን ዩሮ በላይ በቤሊዝ እና ዩራጋይ የተክስ ገንዘብ እንዳሸሹ በመግለጽ የእስፔን ፍርድ ቤት በከፈተባቸው የውንጀል ክስ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የ21ወር እስር እንደተፈረደባቸው ይታወቃል።

በፍርዱ መሰረት እውቁ ተጫዋች ከ21 ወር እስር በተጨማሪ የ2ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት እና አባትዪው ጆርጅን የ1.5ሚሊዮን ዩሮ ካሽ ቅጣት መቅጣቱ ይታወሳል።

ሜሲ ይህንን የፍርድቤቱን ውሳኔ በይግባኝ ሲከራከር ቆይቶ ባለፈው ግንቦት ወር ውስጥ ውሳኔው በድጋሚ እንዲጸና የተወሰነ ሲሆን ሆኖም ሜሲ ይታሰራል ብሎ እንደማይጠበቅ ቢቢሲ አክሎ ገልጻል።

**** አርጀንቲናዊው ሌዮኔል ሜሲ እና ያስመዘገበው ድል-
**በ2017 ሚያዚያ ላይ ለባርሴሎና 500ኛ ግሉን ያስቆጠረ

**ለ5ት ተከታታይ ዓመታት የፊፋ ዎርልድ ባሉን ዲ-ኦር የተባለ ዋንጫ አሸናፊ

**3 ግዜ የአውሮፓ ምርጥ ተጫዋች
** 8ግዜ ከባርሴሎና ጋር ሆኖ የስፓኒሽ ላ ሊጋ ሻምፒዮና
**የእስፓኒሽ ሪኮሪድ ባለቤት
**በ2008 ከአርጀንቲና ጋር ሆኖ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ
**ለአርጀንቲና 55ጎል በማስቆጠር የእስከዛሬ ኮከብ ጎል አግቢነትን
ወዘተ የሚጠቀሱ የሜሲ ድሎች እንደሆኑ ቢቢሲ ዘግባል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ በዚህ ግብርና ታክስ በማጭበርበር ክስ እውቁ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶና እውቁ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪኒሆም በተመሳሳይ መልኩ በታክስና ግብር ማጭበርበር እንደተከሰሱ ዘግባል።