የአሜሪካው ጠፈር መርማሪ [ናሳ]የኤሊየን ግኝትን ይፋ ሊያደርግ ነው

አባይ ሚዲያ ዜና
ወንድወሰን ተክሉ

የአሜሪካው ጠፈር ምርምር ተቃም በምህጻረ ቃሉ ናሳ በቅርቡ የያልታወቁ ፍጥረታትን [ኤሊየን]በአከባቢያችን መኖር ይፋ ያደርጋል ሲሉ ማንነታቸው የማይታወቅ የኢንተርኔት ጠላፊዎችን[ሃከርስ]ምንጭ ጠቅሶ የሩሲያ 24ዜና [RT]ዘገበ።

እንደ የሩሲያ24ዜና ዘገባ -ማንነታቸውን የደበቁት ሃከርሶች ወደ አሜሪካው ናሳ ሲስተም ውስጥ በመግባት ያገኙት መረጃ የጠፈር ተመራማሪው ተቃም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በእጁ የገቡትን የኤሊየንሶችን መረጃ ላይ ተመርኩዘው ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት ለዓለም ይፋ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ዘግባል።

ሆኖም የዜና ጣቢያው ይህንን ዜና ይፋ ለማድረግ በባልታወቁ የኢ-ኔት ጠላፊዎች ሪፖርት ላይ ብቻ ተንተርሶ ሳይሆን የራሱን ተመሳሳይ መጋቢ መረጃዎችን አካትቶበት እንደሆነ ከዘገባው መረዳት ተችላል።

የአሜሪካው ጠፈር ምርምር ተቃም ናሳ-በሚያዚያ ወር 2017 በኮንግረስ ፊት በድርጅቱ ተወካይ ፕሮፌሰር ቶማስ ዙርበቸን [Professor Thomas Zurbuchen, associate administrator for the Science Mission Directorate, told the hearing that NASA’s recent advances, such as the discovery of hydrogen in Saturn’s Moon…]እና በጁፒተር ጨረቃ ላይ ያገኘነው ውቅያኖስ የኤሊየንሶችን በእውን መኖር ለመግለጽ ከመቼውም ግዜ በላይ እጅግ የተቃረብንበት ወቅት ቢኖር አሁን ነው ብለው መናገራቸውንም አያይዞ አቅርባል።

ሃከርሶቹ ሰሞኑን በድህረ-ገጻቸው ላይ በለቀቁት ዜና “ናሳ ኤሌየንሶች እየመጡ ነው” እያለ የተለዋወጠውን የእርሰበርስ መረጃ በመጥለፍ ይፋ አድርገዋል።

የኤሊየን ዜናዎች በመንግስታት ውስጥ በሳይንቲስቶቻቸው አሳሳቢነት ገዝፎ በመምጣቱ የተነሳ የአውሮፓ ጠፈር ምርምር ተቃም [ዮሮ-እስፔስ]በበኩሉ የኤሊየን ፍለጋ ስራ ላይ እንዲሰማራ የሚፈቅድ ፍቃድና በጀት ከአውሮፓ ህብረት እንደተመደበለትና እንደተፈቀደለት ይታወቃል።

ሳይንሳዊ ልቦለድ [ሳይንስ ፊክሽን]እየተባሉ በተለያዩ የሆሊውዱ ፊልሞች ላይ ሲገለጹ የነበሩት የኤሊየንስ ክስተቶች ከሀሳብ ፈጠራነት ልቀው በእውን ያሉ ፍጥረታት ስለመሆናቸው ዜና የምንሰማበት ወቅት እጅግ ቅርብ ነው ሲሉ የናሳ ጠፈር ተመራማሪዎች ገልጸዋል ይላል የሃከርሶቹ ዜና።