ካናዳ የተመሰረተችበትን 150ኛ ልዩ ክብረ በዓል ትውለደ ኢትዮጵያውያንም አድምቀውት አከበሩ

አባይ ሚዲያ ዜና
ወንድወሰን ተክሉ
`

ካናዳ እንደ ሀገር ካናዳ ሆና የተመሰረተችበትን 150 ክብረ በዓል በድመቀት እየተከበረ ያለ ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በበዓሉ ላይ በደማቅ ባህላዊ አቀራረብ በመቅረብ አድምቀውት እንደዋሉ ከተለያየ እስቴት ከተገኘው መረጃ ማወቅ ተችላል።

image

በብሪቲሽ ኮሎምቢያ ቫንኮበር ነዋሪ ከሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ውስጥ አቶ ከበደ አባተ እና አቶ ኦሪዮን መንግስቴ የካናዳን 150ኛ የሀገር ምስረታን ክብረ በዓል በድምቀት ካከበሩት ውስጥ ሆነው የተገኙ ሲሆን ሁለቱም ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቫንኮበር የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ማህበር ውስጥም ንቁ ተሳትፎን በማድረግም የሚታወቁ እንደሆነም ታውቃል።
ካናዳ በ1867 በአራት መስራች ክፍለሀገራት ኦንታሪዩ፣ኩቤክ፣ኒውብራንስ -ዊክ እና ኖቫስኮሻ ሆነው በሀምሌ 1ቀን ካናዳ ብለው ሀገር የመሰረቱበት ቀን ነው ስትል ያብራራችልኝ ደግሞ ሌላዋ ትውለደ ኢትዮጵያዊት ወ/ሮ ናኒ ተስፋዪ ስትሆን በክበረ በዓሉ ላይ በስራ ምክንያት መሳተፍ ባለመቻላ ግን የተሰማትን ቅሬታ ሳትሸሽግ ገልጻለች።

እንደ የቫንኮበራ ወ/ሮ ናኒ ተስፋዪ ገለጻ ዛሬ ካናዳ በአስር ክፍለ ሀገሮች እና በ3 ልዩ ክልሎች አስተዳደራዊ መዋቅር የተዋቀረች ሀገር በመጨረሻ በክልልነት የተካተተችው ነናቪት በ1999 በክፍለ ሀገር ደረጃ ደግሞ የመጨረሻዋ ክፍለ ሀገር ኒውፎንድላንድ እና ላብራዶር በ1949 እንደሆነ ከካናዳ ስነ-ታሪክ መረዳት ተችላል።

ካናዳን መስራቾች አራቱ ክፍለ ሀገሮች ስምምነት ከማድረጋቸው በፊት ሀገሪቱ ምንም አይነት መንግስትና ካናዳ የሚያሰኛት ነገር እንደሌለ የሚነገር ሲሆን አውሮፓውያኑ ፍልስተኞች ከመስፈራቸው በፊት ምድሪቱ ሬድ ኢንዲያንስ በሚባሉ ነገዶች የተያዘች እንደነበረች ከታሪካ ማወቅ ይቻላል።

image
ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ክብረ በዓሉን ሲያከብሩ እኛ በኢትዮጵያዊነታችን
ይህን የካናዳን ልዩ የነጻነት ክብር በዓል ስናከብር ካናዳ በእኛነታችን ተቀብላ ለቀደምት ተወላጆች የሰጠተችውን ሙሉ መብት ለእኛም በእኩል ዓይን በማጎናጸፋ ትልቅ ክብርና ፍቅር ስላለን ሲሉ ተደምጠዋል።