የጎንደር ሕብረት በሲያትሉ የኢትዮጵያ ፌስቲቫል ላይ ሀብታሙ አያሌው የሚገኝበትን ስብሰባ ለዛሬ ጠርቷል

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

የጎንደር ሕብረት አቻዎቹ የጎጃም እና የሸዋ ህብረቶች በሚሳተፉበት ዛሬ ሀምሌ 6 ቀን 2017 በሲያትል ያዘጋጀ ሲሆን ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳና ወጣቱ ሀብታሙ አያሌውን የክብር እንግዶቹ አድርጎ እንደጋበዘ ለማወቅ ተችሏል።

የስብሰባው አጀንዳም በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ እና በአሁኑ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩር ከወጣው የስብሰባው ፕሮግራም መረዳት የተቻለ ሲሆን ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳም በስፍራው ተገኝተው በክፍለ ሀገር ደረጃ የመደራጀትን አስፈላጊነት እንደሚያብራሩ ይጠበቃል።

የጎንደር ሕብረት ማህበር በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል በተፈጠረው ከፍተኛ ጥቃት ምክንያት ህይወታቸው በአደጋ ላይ የወደቀውን የአካባቢውን ህብረተሰብ አቅም በፈቀደ መጠን ለመርዳትና ብሎም የሚረዱትንም ለማስተባበር ዓላምን ይዞ የተቋቋመ የወገን-ለወገን በጎ አድራጊ ድርጅት እንደሆነ ተነግሯል።

የጎንደር እና አካባቢው አውራጃዎች ከባለፈው ሰኔ ወር 2016 ጀምሮ በአግዓዚ ሰራዊት ስር ከፍተኛ በሆነ ወታደራዊ ሃይል ስር እየተረገጠ ያለ አከባቢ ሲሆን ተወላጁም በአብዛኛው እምቢ ለመብቴ፣ እምቢ ለነጻነቴ በሚል ነፍጥ አንስቶ ጫካ በመግባት እየታገለ ያለበት ክልል እንደሆነ ይታወቃል።

የጎንደር ሕብረት በሲያትሉ የኢትዮጵያውያን ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ የራሱን የሆነ ድንኳን ተክሎ ስለዓላማውና እንቅስቃሴው ገለጻን እያደረገ ያለ መሆኑን ከሲያትል የደረሰን ዜና ያስረዳል።