የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ የሚያሳይ ኤግዚቢሽን በጀርመን ኑርነበርግ ከተማ መዘጋጀቱ ተገለጸ

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ ኢትዮጵያውያኖች የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ የሚያሳይ የኤግዚቢሽን ፕሮግራም ማዘጋጀታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቀዋል።

በምህጻረ ቃል (አክዋባ) በመባል የሚታወቀው መንግሳታዊ ያልሆነ ድርጅት ይህንን ኤግዚቢሽን በኑረንበርግ ከተማ እንዳዘጋጀ ታውቋል።

ይህ ድርጅት (አክዋባ) ዘርን ሃይማኖትን እና የፓለቲካ አመለካከትን ታሳቢ ሳያደርግ በጀርመን ኑረንበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖችን በአንድነት የማሰባሰብን አላማ ይዞ እንደተቋቋመ ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያኖች በዚህ ድርጅት በመሰባሰብ በተለያዩ ዝግጅቶችና መድረኮች ባህላቸውን ያስተዋውቃሉ እርስ በእርስም ያላቸውን ማህበራዊ ግኑኘነታቸውንም ያጠነክሩበታል።

በነገው እለት በሚደረገው ዝግጅት ዲዛይኑ በኢትዮጵያውያኖች የተቀረጸና የኢትዮጵያን ገጽታ የሚያሳይ ልዩ ተገጣጣሚ ድንኳን በዚሁ የጀርመን ከተማ እንደሚቆም ለመረዳት ተችሏል።

ይህ ልዩ ተገጣጣሚ ድንኳን መላመድ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በዚሁ እለት ኢትዮጵያውያኖች ይህን ድንኳን ይገጣጥማሉ።

በዚሁ ዝግጅት ላይ እንድትታደሙ የፕሮግራሙ አዘጋጆች የአክብሮት ግብዣቸውን ያቀርባሉ።

ፕሮግራሙ የተዘጋጀበት ቦታ:- Villa Leon Philipp koerber -weg 1, 90439 Nürnberg

                            :-ሰአት ከረፋዱ 10 ሰአት ጀምሮ

                           :-በ ጁላይ 9 ቀን 2017 እኤአ

                   አዘጋጅ :- Äthiopischer Kulturverein in Nürnberg e.V.