አርቲስት ሐመልማል ተሳስተን ነው ይቅር መባባል አለብን በማለት ይቅርታ ጠይቃለች (Video)

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ ከጀመረበት ከ1984 ዓም ጀምሮ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፖ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብ ባህላቸውን ለልጆቻቸው ከማስተላለፍ አልፈው ለሌላው የዓለም ሕዝብ እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

34ኛውን ዓመታዊ የስፖርት እና የባህል ዝግጅት በሲያትል ዋሽንግተን በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ እንደሚገኝ የአባይ ሚዲያን የቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉ በተለያየ የአለማችን ክፍል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገለጹ።

አርብ ማምሻው በነበረው የሙዚቃ ፕሮግራም ላይ አርቲስት ሐመልማል አባተ ህዝብ በተሰበሰበበት እንኳን ደህና መጣቹ እኔ ወደ እዚህ ከተማ በ14 አመቴ ነው የመጣሁት ብላ ንግግሯን በመጀመር ሁል ጊዜ ሰው ሲሰራ ይሳሳታል አርቲስት እህት እና ወንድሞቼ ባይወክሉኝም ስሜታቸውን ስለማውቅ እባካችሁን እኛ አንድ ነን አንድ የሚያደርገን ኢትዮጵያዊነታችን ነው ስለዚህ እንነጋገር ከተነጋገርን ለዚህ ሁሉ ችግር ባልደረስን ነበር። ተሳስተን ነው ይቅር መባባል አለብን በማለት ይቅርታ ጠይቃለች።

ቪዲዮውን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጫኑ።