ጋና የመጀመሪያዋን ሳተላይት ወደ ህዋ በተሳካ መንገድ አመጠቀች

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

የምእራብ አፍሪቃዊዋ አገር የሆነችው ጋና የተሳካ የህዋ ሳተላይት መንኮራኩር ለማምጠቅ እንደቻለት ተዘገበ።

ከ ኦል ኔሽን ዩኒቨርስቲ የተውጣጡ ተማሪዎች ተገንብታ ጋናሳት 1 የሚል ስያሜ የተሰጣት መንኮራኩር ከአለም አቀፉ የምህዋር ማእከል ወደ ህዋ እንድትመጥቅ ተደርጋለች።

ይህንን ፕሮጀክት ለመፈጸም ሁለት አመታትና ወደ 50,000 የአሜሪካ ዶላር እንደፈጀም ተነግሯል። የጃፓን መንግስት ለዚሁ ፕሮጀክት እርዳታ እንዳደረገም ተገልጿል። ጋና በዚህ ባመጠቀችው ሳተላይት ድንበር ለማካለል የሚጠቅማትን መረጃ መሰብሰብ ያስችላታል ተብሏል። በተጨማሪም የአገሪቷን የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሏል።

በህገወጥ የማእድን ማውጣት ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን ድርጅቶች አሊያም ግለሰቦችን ለወደፊቱ በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችላል በማለት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ተናግረዋል።