ዩኔስኮ የአስመራን ከተማ የዓለም ቅርስ ብሎ መዘገበ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህልና ቅርስ ክፍል ዩኔስኮ/Unesco የኤርትራን ዋና ከተማ በቅርሳዊ ከተማነት መመዝገቡን ቢቢሲ አስታወቀ።

እንደ ዩኔስኮ አገላለጽ ሰሜናዊቷ የቀይ ባህር ሀገረ ኤርትራ በዋና ከተማዋ አስመራ የዓለም ህዝብ በታሪካዊ ቅርስነት ሊመዝግባቸውና እውቅና ሊሰጣቸው የሚገባቸው ድንቅ የአርክቴክቸር ንድፍ ውጤቶች የሆኑ በርካታ ህንጻዎች ባለቤት ናት ብሏል።

የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ይህን በዓለም አቀፉ የመንግስታት ድርጅት የቅርስና ታሪክ ክፍል [Unesco] እውቅና ያሰጣትን የአርክቴክት ውጤቶችን መገንባት የቻለችው ሀገሪቷ በጣሊያን ቅኝ ግዛት ስር በነበረበችበት ከ1889-1941 ባለው ጊዜ ውስጥ በጣሊያናውያኑ አርክቴቸሮች የተገነቡ ህንጻዎች መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

image

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገር በሀረ-ነጋሽ የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈተታኑ የውጭ ሀይሎች መውጪያና መግቢያ በመሆን ለረዥም ዘመናት ከፍተኛ የአርበኝነት ተጋድሎና መስዋእትነት የተከፈለባት የኢትዮጵያ አካል የነበረች ስትሆን፣ በ1889 በወራሪዋ ባህረ-ነጋሽ የሚለው ስያሜ ኤርትሪያ ወደሚለው አዲስ መጠሪያ የተለወጠች ሀገር ነች። ክፍለ ሀገሪቷ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተሸናፊ ከሆነችው የወራሪዋ ጣሊያን እጅ ወጥታ ነጻ ሀገር ትሁን ወይም ወደ እናት ሀገሯ ትመለስ አሊያም በኮንፌዴሬሽን ትዋሃድ በሚለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሪነትና ተቆጣጣሪነት በተካሄደ ሬፈረንደም የኤርትራ ህዝብ በኮንፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር እንዲዋሃድ ብለው በከፍተኛ ድምጽ በመምረጥ ከኢትዮጵያ ጋር የተዋሃደች ሀገር ነበረች። ከ10 ዓመት ቆይታ በኋላ በእነ ተድላ ባይሩና የሳባጋዲስ የአንድነት ሃይሎች ኤርትራ ከእናት ሀገሯ ኢትዮጵያ ጋር በኮንፌዴሬሽን ሳይሆን በውህደት አንድ መሆን አለባት የሚል ጥያቄን በወቅቱ ለነበሩት የኢትዮጵያ ገዢ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በማቅረባቸው ንጉሱ ፌዴሬሽኑን አፍርሰው የውህደት አዋጅ ማወጃቸው ይታወቃል።

image

ሆኖም ይህን የውህደት እርምጃ የተቃወሙ የኤርትራ ተቃዋሚ ሀይል ጀብሀ በፌዴሪሽኑ መፍረስ ተቃውሞ አመጽ የጀመረ ሲሆን የተጀመረውም አመጽ ሻእቢያን ወልዶ 30 ዓመት የፈጀ የእንገንጠል አትገነጠሉም ከፍተኛ ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ በህወሃት አጋዥ አማጺ ሃይል አዲስ አበባ ያለው ማእከላዊ መንግስት በ1991 [1983] ሲፈርስ ነጻነቷን የተቀዳጀች ሀገር ስትሆን በ1985 [1993] በተካሄደ “ነጻነት ወይስ ባርነት” ምርጫ ሬፈረንደም የኤርትራ ህዝብ ነጻነትን በመምረጥ ሉዓላዊ ሀገር በመሆን በአፍሪካ ከደቡብ ሱዳን ቀጥላ ወጣቷ ሀገር እንደሆነች የሚዘነጋ አይደለም።

image

ወጣቷ ሀገረ ኤርትሪያ በ1889-1941 ባለው የቅኝ ግዛት ዘመን በቅኝ ገዢዋ ኢጣሊያ በተገነቡት ድንቅ የአርክቴክት ህንጻዎች ምክንያት ዋና ከተማዋ አስመራ በዓለም አቀፍ የቅርስ ከተማነት ለመመዝገብ የቻለች ሀገር ነች።