የአውሮፓው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌደሬሽን በተዘዋዋሪ የሚመራው በወያኔዎች መሆኑ ተጋለጠ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

ከሀምሌ 26 ቀን 2017 እስከ 29/07/2017 ሮማ ሊካሄድ የታቀደው የአውሮፓው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌደሬሽን የዝግጅቱን ሂደት ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ነዋሪነቱ ኢትዮጵያ የሆነውና የአበበ ቢቂላ ስፖርት ማህበር ሊቀ መንበር የሆነው ዮናስ ሃጎስ መሆኑ ተነገረ።

አቶ ሃብታሙ ጥቁማ የተሰኘው ግለሰብ ነዋሪነቱ ሮማ ሲሆን ለዚህ ዝግጅት የሙሉ ስዓት ሰራተኛ እንዲሆን በአቶ አንድነት ክፍያ የተቀጠረ መሆኑን እና የግለሰቡ አባት አቶ ጥቁማ ዳባ ደግሞ የወያኔ አምባሳደር በሮማ ታማኝ ሾፌር መሆናቸው ተደርሶበታል።

ለማስታወስ ያህል፣ የሰሜን አሜሪካው የኢስፋና ዝግጅትም በቱጃሩ ሼህ መሃሙድ እላሙዲን ሊበተን ታስቦ እንደነበር ይታወቃል። ሆኖም ግን በቁርጥ ቀን ልጆች የሼሁ ሴራ ከሽፎ እነሆ ያማረና የደመቀ ብሎም ሰንደቃችን በፓራሹት በክብር የወረደበት ዝግጅት ተዘጋጅቶ አይተናል ሲሉ ከአውሮፓ መረጃውን ያሰራጩት ገልጸዋል።

ጽሁፉን ያሰራጩት ወገኖች፣ ወገኔ ሆይ የህወሃትን ሴራና ተንኮል ከአንድነታችንና ከኢትዮጵያዊነታችን ልናስወግደው ይገባል በማለት መረጃውን ሁሉም እንዲያዳርሰው ጠይቀዋል።