ኢትዮጵያ ከአሜሪካ እርዳታ ከሚያገኙት አፍሪካ አገራት መካከል አልተመደበችም

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ኢትዮጵያ አሜሪካ ከምትለግሰው $639 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደማይደርሳት የአሜሪካ እርዳታ ሰጭ ተቋም (USAID) ገልጿል።  እርዳታው ምግብ እጥረት ላለባቸውና ጦርነት ለተከሰተባቸው አገራት የተመደበ ነው።

የአሜሪካ እርዳታ ሰጭ ተቋም (USAID) እንደገለጸው እርዳታው ወደ አራት አገራት የሚላክ ነው። የተመደበላቸው አገራት ደቡብ ሱዳን፣ ናይጄሪያ፣ ሶማሊያ እና የመን ናቸው።

የአሜሪካ እርዳታ ሰጭ ተቋም (USAID) መግለጫ እንደሚለው እርዳታው ለአስቸኳይ ምግብ እርዳታ፣ የነፍስ አድን ህክምና፣ ጽዳት፣ አስቸኳይ መጠለያ እና ስደተኞችን ለማስተናገጃ ይውላል። በማከልም የአሜሪካ ንጹህ ውሃ እንዲዳረስ፣ የግል ንጽህና እንዲጠበቅ፣ ኮሌራን የመሰሉ ተላላፊ በሽታዎች እንዳይዛመቱ በልግስናው የታለመ ሲሆን ዛሬ ኮሌራ በዓለም ሁሉ ባልታየ መንገድ የተስፋፋባትን የመንን ጨምሮ ያተኮረ ነው።

የአሜሪካ እርዳታ ሰጭ ተቋም (USAID) እንደሚለው ኮሌራ እንደ የመን ባይሆንም በኢትዮጵያም ዛሬ አሳሳቢ ነው።

ሚስተር ሮብ ጄንኪንስ የአሜሪካ እርዳታ ሰጭ ተቋም (USAID) የዴሞክራሲ፣ ግጭቶችና ሰባአዊ እርዳታ ቢሮ አላፊ ሲናገር “እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንገኛለን። ደቡብ ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እርዳታ ይሰጣቸው እንደተባሉት አራት አገራት አይሆንም። ትኩረት ካልተሰጠው ወደከፋ ሁኔታ ሊሻገር የሚችል ነው” ብሏል።

አሜሪካ በዚህ ዓመት $252 ሚሊዮን ለኢትዮጵያ በእርዳታ መልክ ሰጥታለች።

የዜና መነሻ የሆነው $639 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ በአውሮፓ አገራት (G20 summit) መካለል ያለፈው ሳምንት ሃምበርግ ጀርመን ላይ በተደረገ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለስራ በተገኙበት ስብሰባ የተወሰነ ነው።

አባይ ሚዲያ በዚህ ጉዳይ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተንታኞች ይህ የአሜሪካ ውሳኔ የቀድሞው የባራክ ኦባማ አስተዳደር ያደርገው ከነበረው ለየት ያለ የኢትዮጵያ መንግስት በህዝብ ላይ የሚወደውን ኢሰባዊ እርምጃዎች መኮነኛ መንገድም ሊሆን ይችላል በማለት አሳባቸውን ሰንዝረዋል።