የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 5 ለ 1 በሆነ ስፊ ጎል አሸነፈ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በመጪው ዓመት 2018 በኬኒያ አስተናጋጅነት ለሚካሄድው የቻን ሻምፒዮና ማጣሪያ ከጅቡቲ ጋር ባደረገው የማጣሪያ ውድድር 5-1 በሆነ ሰፊ ጎል ማሸነፉን የአማራ ቴሊቪዥን ዘገበ።

ቡድናችን ከሜዳው ውጭ ተጋጣሚውን በሰፋ ጎል ሲያሸንፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ በጅቡቲ ላይ የተቀዳጀው ድል የመጀመሪያው ሲሆን ውጤቱም ቡድኑን ከምድቡ የማጣሪያውን ውድድር በጥሩ ነጥብ እንዲያጠናቅቅ እንደሚረዳው ይታመናል።

ለቡድናችን 4ቱን ጎሎች ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ ሲሆን ቀሪዋን ደግሞ ሙሉዓለም መስፍን በጉሌድ እስታዲየም እንዳስቆጠራት ለማወቅ ተችሏል።

ቻን በየዓመቱ በካፍ አዘጋጅነት የአፍሪካን እግር ኳስ ደረጃ ለማሳደግ ተብሎ የሚዘጋጅ ሻምፒዮና ሲሆን በውድደሩ የሚሳተፉ ተጫዋቾች በሀገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበትና ፕሮፌሽናሎቹ የማይሳተፉበት እንደሆነ ይታወቃል።