በአውሮፓ ያሉ ኢትዮጵያውያን በኢጣሊያ ሮም በሚካሄደው ፌስቲቫል ላይ መሳተፍ አይገባንም አሉ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በአውሮፓ የኢትዮጵያ እስፖርትና ባህል ፌስቲቫል በመንግስት ቁጥጥር ስር ሆኖ ዘንድሮ በሮም በሚካሄደው ዝግጅት አንሳተፍም ሲሉ ኢትዮጵያውያኑ ከአውሮፓ ለአባይ ሚዲያ ገለጹ።

image

የመንግስት እጅ ባዘገጀው ፌስቲቫል መገኘት አይገባንም ያሉት እነዚህ ኢትዮጵያውያን ማህበራችንን ግን መልሰን መውሰዳችን አይቀሬ ተግባር ነው ብለው እስከዚያ ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አድርገዋል።