ስድስቱ የዓረብ ሀገራት ፊፋ የ2022 የዓለምን ዋንጫ አዘጋጅነት ከካታር እንዲነጥቅ ጠየቁ

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

ባለፈው ወር ከካታር ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ያቋረጡት ስድስቱ የዓረብ ሀገራት ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ 2022ን የዓለም ዋንጫ አዘጋጅነት ከካታር እንዲነጥቅ መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘገበ። ስድስቱ የዓረብ ሀገራት ሳኡዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ ባህሬን፣ የመን፣ የተባባሩት ኤምሬትስ እና ሞሪሺየስ መሆናቸውን ሮይተር ጠቅሶ ምክንያታቸውንም ሲገልጹ ካታር አሸባሪዎችን በመርዳቷ አካባቢው በሽብር መወጠሩን በመግለጽ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል። ሆኖም ሮይተርስ የስድስቱ ዓረብ ሀገራት ደብዳቤ  ኮፒ እንዳልደረሰው ጠቅሶ የፊፋው ፕሬዚዳንትም ደርሶኛል አለማለታቸውን ከቃለ አቀባዩ በኩል እንደተነገረው አብራርቷል።