መንግስት አልባዋ ሶማሊያ እና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

መንግስት አቆማለሁ ብላ በምትውተረተረዋ ሶማሊያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በንግድ ስራ ላይ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል ሲል ሬውተርስ የዜና ወኪል ዛሬ ዘገበ።

ባህር ለባህር የተዘረጋ የስልክ ሽቦ በመበጠሱ ምክንያት ሶማሊያ በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ተይዛ ቆይታለች። በመሆኑም የንግድ ተቋሞችን ኗሪዎች በችግር ላይ ወድቀዋል። በነበረው ችግር ላይ ሌላ ችግር ድርርቦሽ መሆኑም ታውቋል።

ሚስተር አብዲ አንሹር የሶማሊያ የፖስታና ቴሌኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ከወር በፊት አንድ የንግድ መርከብ ባህር ውስጥ ያለ የስልክ መስመር በመበጠሱ ችግር መፈጠሩን አስረድቷል። አደጋው ሶማሊያን ከዓለም የስልክና ኢንተርኔት ግንኙነት የለየ ነበር።

የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል ወይም አማራጭ መፈለግ ነበረባቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርታቸው ተስተጓጉሏል። ሚኒስትሩ እንደገለጹት ሶማሊያ በዚህ አደጋ ብቻ በግምት $10 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶባታል።

ሞሃመድ ኑር የተሰኘ ነዋሪ “ኢንተርኔት የተቋረጠ ማታ የለት እንጀራየን አጣሁ” ብሏል። ኑር በወር $500 ዶላር ገቢ ነበረኝ ዛሬ ሲጋራና ዳቦ ከወዳጆቼ እለምናለሁ ብሏል።

የሶማሊያ ኢኮኖሚ ገና እንየተንሰራራ ነው። ይህ የሆነው የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች አሸባሪውን አል ሸባብን ከሞቃዲሾ እንዲወጣና እንዲዳከም ካደረጉ ወዲህ ነው። የአሸባሪው አል ሸባብ ጥረት በምእራብ ሃይሎች የተደገፈውን መንግስት ለመጣል ነው። አል ሸባብ ዛሬም አደጋዎች የሚጥል ነው።

በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት ወጣቶች ስራ ፈተዋል። በየሻይ ቤቶች ሰዓታት በከንቱ ያሳልፋሉ። ሞሃመድ አህመድ ሃሬድ ሶማሊ ኦፕቲካል ኔትውርክስ (Somali Optical Networks (SOON) የተሰኘ ተቋም የንግድ አስተዳዳሪ ነው። በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት አንድ ሚሊዮን ዶላር በቀን ከስሬአለሁ ሲል ይናገራል። ሞሃመድ አህመድ ሃሬድ ደንበኞች በኢንተርኔቱ መቋረጥ ካጧቸው ግልጋሎቶች መካከል ፓስፖርት ቶሎ አለማግኘትና የኤለትሮኒክ የአየር በረራ ቲኬት አለማግኘት ይገኙበታል።

የሶማሊያ ብሄራዊ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የከፍል ትምርታቸውና የሚሰሩዋቸው ምርምሮች መስተጓጎላቸውን ተናግረዋል። ፌስቡክ ዩ ቲዩብን እና ጉግልን የመሳሰሉ ዜና እና መረጃ ማግኛ መንገዶች ተዘግተውባቸው ቆይተዋል። ለአደጋው መድረስ የነዚህን መረጃ ማግኛ መንገዶች መዘጋት አክራሪ እስልምና ተከታዮችና ኋላ ቀሮችን ደግሞ በተቃራኒው አስደስቷል።