በዘንድሮው የIAAFU18Nairobi ሻምፒዮና የመዝጊያ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ በ3000ሜ ወርቅ አገኘች

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

የዘንድሮውን IAAFU18Nairobi አስተናጋጇ ኬኒያ ትናንት በነበራት ዘጠኝ ሜዳሊያዎች ላይ ዛሬ በመዝጊያው እለት ስድስት ሜዳሊያዎችን በመውሰድ በኢትዮጵያ ተይዞ የነበረውን የ4ኛነትን ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ስትደመድም ኢትዮጵያ ሶስት ሜዳሊያ በማከል ውድድሩን በ5ኛነት ደረጃ አጠናቃለች።

በዛሬው የመዝጊያ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰለሞን ቢረጋ በ3000 ሜትር አንድ ወርቅና ሁለት የነሀስ ሜዳሊያ በማከል በአጠቃላይ ውድድር 4 ወርቅ 3 ብር እና 5 የነሀስ ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን በ5ኛ ደረጃ ለማጠናቀቅ ችላለች።

የኬኒያ ቡድን በሜዳው ትናንት ገጥሞት የነበረውን ሽንፈት በሚክስ መልኩ ዛሬ 6 ሜዳሊዎችን በማግኘት በአጠቃላይ 15 ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን በ4ኛነት ሲጨርስ ደቡብ አፍሪካ በ1ኛነት፣ ቻይና በ2ኛነት እና ኩባ በ3ኛነት ደረጃ በመያዝ ውድድሩ ተጠናቋል።