በምእራብ ኦሮሚያ ለ3ኛ ቀን የስራ አድማው እንደቀጠለ ነው ከሆሎታ እስከ ወለጋ መንገድ ተዘግታል

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

ዛሬ ረቡእ በምእራብ ኦሮሚያ፣ከሆሎታ እስከ ወለጋ ደምቢ ዶሎ ያለው መንገድ ለትራፊክ ዝግ እንደሆነ የተገለጽ ሲሆን የንግድ ተቃማት፣መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ መ/ቤቶችም ካለምንም ስራ ተዝግተው እንዳሉ ከስፍራው ካሰባሰብነው መረጃዎች መረዳት ተችላል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እኩለ ቀን ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀምራል ብለው የሰጡትን መግለጫ ለማጣራት ወደ አምቦ እና ጊንጪ ከተሞች ባደረግነው ጥያቄ ከነዋሪው የተሰጠን መልስ ከአስኮ ጀምሮ ቡራዩ፣ገፈርሳ፣ሆሎታ፣ኦሎንኮሚ፣ጊንጪ፣አምቦ፣ጉደር፣ሸኖ፣ለቀምትና ደምቢ ዶሎ ድረስ አንዳችም የትራንስፖርት አገልግሎት አለመጀመሩን ተናግረው በመንግስት በኩል ግን ህዝቡን አስፈራርቶ ስራ ለማስጀመር ባልሰልጣናቱ ሙከራ ሲያደረጉ ነበር ብለዋል።

image

በወሊሶ ያለውም የስራ ማቆም አድማ ዛሬ በሶስተኛው ቀንም እንደቀጠለ ነዋሪዎቹ ገልጸው፣ በመንግስት በኩል ታቅዶ የነበረው ስብሰባም ሳይካሄድ ቀርታል ብለዋል።

በምእራብ ኦሮሚያ ዞን እና በጂማ፣በፍቼ እና በምስራቅ ሀረርጌ ያሉ ነጋዴዎች በመንግስት በኩል የተመደበብን የዚህን ዓመት ግብር ተመን ከእለት ተእለት ገቢና ወጪያችን ጋር የማይጣጣምና እጅግ የተጋነነ ነው በማለት መቃወም መጀመራቸውን ቀደም ብለን መግለጻችን ይታወሳል።
`