የሱማሌው አልሸባብ በዓመት ከ150ሚሊዩን ዶላር በላይ ከነጋዴው ይሰበስባል ተባለ

FILE - In this Thursday, Feb. 17, 2011 file photo, al-Shabab fighters march with their weapons during military exercises on the outskirts of Mogadishu, Somalia. Foreign military forces carried out a pre-dawn strike Saturday, Oct. 5, 2013 against foreign fighters in the same southern Somalia village where U.S. Navy SEALS four years ago killed a most-wanted al-Qaida operative, officials said. (AP Photo/Mohamed Sheikh Nor, File)

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በሱማሊያ ያለው አሸባሪ ድርጅት አልሸባብ በዓመት ከ150$ሚሊዮን ዶላር በላይ ነጋዴዎችን እያስፈራራ ይሰበስባል ሲል የሱማሌ መንግስት ደህንነት ሃላፊ ገለጹ።
እንደ አቶ አብዱላሂ ሞሀመድ አሊ አባባል አሸባሪው ቡድን ነጋዴዎችን እያስፈራራ በግድ ግብር እና ቀረጥ እንደሚሰበስብ የገለጹ ሲሆን ከፋዮቹ በማእከላዊው መንግስት እና በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ቁጥጥር ስር ካሉት የሞቃዲሾና የኪስማዩ ከተሞች ነዋሪዎችም ናቸው ብለዋል።

ነጋዴዎቹ በመንግስት ቁጥጥር ስር ባለግዛት ውስጥ ሆነው ለአሸባሪው ቡድን ዛቻ ተበግረው በድብቅ ወርሃዊ ክፍያ እንደሚፈጽሙ የተደረሰበት ሲሆን ከፋዮቹ ክፍያውን በኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ማዘዋወሪያ መንገድ፣በሃዋላ እና ብሎም በእጅ ለእጅ ክፍያውን እንደሚፈጽሙ ተገልጻል።
የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል ከ20ሺህ በላይ ሰራዊቱን በሱማሊያ ያሰማራ ቢሆንም አሸባሪውም ዋና ዋና ከተሞችን ለቆ ወደ ደቡባዊው የሱማሊያ ገጠራማ ክልል የተዛወረ ቢሆንም በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ የሚያደርሰውን ጥቃት ግን ከመፈጸም እንዳልተገታ ይታወቃል።