ዘግናኙ በሶማሊያ እየተከሰተ ያለው አስፈሪ ሁኔታ በኦጋዴንም አለ ተባለ

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ህወሃት በመለስ ዜናዊ መሪነት ሶማሊያ ዘው ብሎ ሲገባ የምእራቡን ተቀባይነት ለማግኘት ብሎ ነበር። ይህን ብልጣብልጥነት ምእራባውያን በጊዜ ትምህርት እንዲያገኙ ስላደረገ ህወሃት መራሹ መንግስት ለአካባቢው ሰላም አደፍራሽ ሃይል እንጂ ሰላም አምጪ እንዳልሆነ ዛሬ በግልጥ ይታያል። ሶማሊያ ያለው ረሃብ ኢትዮጵያ አገራችንም ታፍኖ እንጂ በኦጋዴን መኖሩን መካድ አይቻልም። ዘግናኙ በሶማሊያ እየተከሰተ ያለው አስፈሪ ሁኔታ በኦጋዴንም አለ።


ዘግናኙ በሶማሊያ እየተከሰተ ያለው አስፈሪ ሁኔታ

ባይዶዋ፤ ሶማሊያ ከአሸባሪው ጽንፈኛ የታጠቀ ቡድኑ አል ሸባብ ነጻ ወጣች የተባለው ከአምስት ዓመታት በፊት ቢሆንም “ነፃ መውጣት”፡ የሚባለው ለይስሙላ ነው ይላል አንድ የዋሽግቶን ፖስት ተወካይ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥበቃና የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ቦታው ያሰማራው ሃይል ካለበት አስር ማይል ወጣ ብሎ ግዛቱ የአሸባሪው አልሸባብ ነው።

አል ሸባብ በተቀነባበረ ቪዲዮ ትእይንት በጎን መንግስት መስርቻለሁ ቢልም የሚያምነው የለም። የታወቀው ነጋዴውን ግብር ክፈለኝ በማለትና ሳይታሰብ ሰው በመግደሉ ብቻ ነው።

ምእራቡ ዓለም በተለይ አሜሪካ አዲሱ የሶማሊያ መንግስት ስር ሰዶ ጠንክሮ እንዲቆም ፍላጎቱን እያሳየ ነው። የመንግስቱ መሪ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ሶማሊያዊ አሜሪካን የሆኑና የሁለት አገር ዜግነት ያላቸው ናቸው። ወደ ስልጣን ከመሄዳቸው በፊት በባፋሎ ግዛት ኒው ዮርክ የህዝብ መገናኛ ሚኒስትር ሰራተኛ ነበሩ።

የአሜሪካ ፍላጎት መንግስት በሶማሊያ እንዲቆም መርዳት ብቻ ሳይሆን የሶማሊያ ህዝብ የኑሮ ምቾት ላይ ማተኮርም አለበት። ዛሬ ሶስት ሚሊዮን ወይም ከሶማሊያ ህዝብ ብዛት አንድ አራተኛው እርዳታ ፈላጊ ነው። ድህነትና ተስፋ መቁረጥ አሸባሪነትን አያመጡም፤ አሸባሪነት ሊስፋፋ የሚችልበትን ሁኔታ ሊጋብዙ ግን ይችላሉ።

እንግዳ ደራሽ ሆነው የሚመጡ አደጋዎች ለምሳሌ የመሬት መንቅጥቀጥ፤ ከባህር ተነስቶ መሬትን የሚያጠፋ ከባድ ማእበል (ኸሪኬን) ሲከሰቱ ጊዜያዊ ለጋሽነትን ያመጡና ወዲያው ደግሞ አደጋው ይረሳል። ቀስ ብለው የሚነዱ ግጭቶች እንደ ደቡብ ሱዳን፣ ሰሜን ናጄሪያ፣ የመን እና ሶማሊያ ያሉት ናቸው። ሰለእነዚህ ብዙ ድምጽ አይሰማም።

በሚያሳዝን መንገድ ጠኔ የያዛቸውን ህጻናት በባይዶዋ ማየት አስፈሪ ነው። ሰው የታጎረበት፤ በሙቀት የታፈነው ሆስፒታል ውስጥ የሚታየው ይህ ነው። ዘግናኙ በሶማሊያ እየተከሰተ ያለው አስፈሪ ሁኔታ በአኦጋዴ ኢትዮጵያም አለ።

ሶማሊያ ዛሬ ጊዜያዊ ሃዘኔታ ሳይሆን ዘላቂ እርዳታን ትሻለች። ኢትዮጵያም ከቅሚያ ይልቅ ህዝብ ለችግሩ የሚደርስለት መንግስት ሊኖራት ካልቻለ እንደ ሶማሊያ ካለው አደጋ ልትላቀቅ አይቻላትም።