በሩሲያ ጉዳይ የዶናልድ ትራምፕ አማች ዛሬ ቃላቸውን ሊሰጡ ነው

Jared Kushner, senior White House adviser, attends a meeting between U.S. President Donald Trump, not pictured, with House and Senate leadership in the Roosevelt Room of the White House in Washington, D.C., U.S., on Tuesday, June 6, 2017. Trump is bringing lawmakers to the White House in hopes of kick-starting his legislative agenda while Washington focuses on the latest twists and turns in the Russia investigation. Photographer: Olivier Douliery/Pool via Bloomberg

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ ኢቫንካ ትራምፕ ባለቤት ጃሬድ ኩሽነር ዛሬ በመወሰኛው እና መምሪያው ምክር ቤት አቢይ ኮሚቴ ፊት ቀርበው በፕሬዚዳንቱ እና በሩሲያ ምስጢራዊ ግንኙነት ላይ ቃላቸውን እንዲሰጡ መታዘዙ ቪ.ኦ.ኤ ገለጸ።

በሩሲያና በትራምፕ መካከል ምስጢራዊ ግንኙነት አለ የሚለውን ክስ እየመረመረ ካለው የምክር ቤት እና የአቃቤ ህግ መርማሪ ኮሚቴ ሌላ የመወሰኛው እና የመምሪያው ምክር ቤት አቢይ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ የታዘዙት የፕሬዚዳንቱ አማች በትራምፕ ምርጫ ግብረ ሃይል ውስጥ በአማካሪነት የሰሩ በመሆናቸውና የሩሲያውን አምባሳደር ለአራት ግዜ ያህል ስለተገናኛቸው ነው ተብሏል።

የኢቫንካ ትራምፕ ባለቤት እና አክራሪ የአይሁድ እምነት ተከታይ የሆኑት ጃሬድ ኩሽነር ባለፈው ቅዳሜ የአምባሳደርነት ስራቸውን በፍቃዳቸው ከለቀቁት በዋሽንግተን የሩሲያ አምባሳደር ሰርጌ ጋር ለአራት ግዜ እንደተጋናኙ የተጋለጠ ሲሆን ግንኙነቱን ግን ቀደም ሲል እንዳልተፈጸመ አድርገው ሲክዱ እንደነበር አይዘነጋም።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2016ቱ ምርጫ ፉክክር ተፎካካሪያቸውን ወ/ሮ ሂላሪ ሮድሃም ክሊንተንን ለመሸነፍ የሚረዳ መረጃን ከሩሲያ ተቀብለዋል ተብለው የተከሰሱ ሲሆን ክሱን ግን ፕሬዚዳንቱ መሰረተ ቢስ ብለው ማጣጣላቸው ይታወቃል። ሆኖም በምክር ቤቱ እና በጠቃላይ አቃቤ ህግ የተያዘ ምርመራ በጉዳዩ ላይ ኮሚቴ አቃቁሞ እየመረመረ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ንኪኪነት አላቸው የተባሉትንም እየጠራ ቃላቸውን እየተቀበለ እንደሆነም ይታወቃል።

የፕሬዚዳንቱ አማች ጃሬድ ኩሽነር በምርጫው ወቅት የፕሬዚዳንቱ የምርጫ አማካሪ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በዋይት ሃውስ የፕሬዚዳንቱ የመካከለኛው ምስራቅ ፖሊሲ አማካሪነት ተሾመው እየሰሩ ያሉ መሆናቸው ይታወቃል።