ገንዘብዎን ለወያኔ ባለመስጠት ለወገንና ቤተሰብዎ አጋር ይሁኑ! ! (ጅግሳው ነኝ ከኖርዌይ)

15ኛው የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን የወያኔ መሆኑ ተደጋግሞ የተገለጸ እውነት ነው። እርስዎ ቀደም ብለው ባቀዱት መሰረት ጉዞዎን መሰረዝ ካልቻሉ በዝግጅቱ ሜዳ ላይ ሳይገኙ ጊዜዎን የሚያሳልፉባቸው በርካታ አማራጮች አሉልዎት። የጥንታዊቷን ሮማ ታሪካዊ ስፍራዎችንና የቫቲካንን መንፈሳዊ ስፍራ በመጎብኘት ጊዜዎን የማያስቆጭ ማድረግ ይችላሉ። ዝግጅቱ በወያኔ ቁጥጥር ስር መሆኑን እያወቁ ማድረግ ያልብዎት እርምጃ ቢኖር ግን ለዚህ ዝግጅት ገቢ ከሚያስገኙ ሁነቶች ራስዎን ገድበው ለገዛ ቤተሰብዎችዎ መግደያ ጥይት መግዣ እንዳይሰጡ መጠንቀቅ ነው። መወሰድ ከሚገባቸው ርምጃዎች መካከል፡

 በተቻለ መጠን ወደ ሜዳው መሄድን መቀነስ ወይም ሁኔታውን ልመልከተው ብለው ካሰቡ ካሉት ቀናት ውስጥ በአንዱ ብቻ በመገኘት ያለውን ድባብ መገምገም ይችልሉ። በዚህም በየቀኑ የመግቢያ ዋጋ በመክፈል ለወያኔ ኤምባሲና ለትግራይ ልማት ማህበር የሚያስገኙትን ገቢ ይቅንሳሉ።

 ሜዳው ላይ ከገቡ በኋላም የሚያወጡትን ወጪ ቆጠብ ማደረግ፡ እንዲሁም ከማነው ነገሮችን የምገዛው ብለው በማሰብ የወያኔና ተላላኪዎቹ በሆኑ የንግድ ስራዎች ላይ የራስዎን ተአቅቦ ማድረግ፣

 ይህ ዝግጅት ገና ከመነሻው ሮማ ላይ ሲወሰን ወያኔን ለመጥቀምና የነጻነት ድምጽ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ክፍል ለማግለል መሆኑን በመረዳት በከተማው ውስጥ የሚደረጉ የነጻነት ተቋማት ዝግጅቶች ላይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ ማድረግ፣

 ይህ መረጃ ለሁሉም እንዲዳረስ ማድረግና ሌሎችም ወገኖች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ መምከር።

እነዚህ ማንም ሳያስገድድዎት እራስዎ ሊወስዱዋቸው የሚችሉዋቸው እርምጃዎች ናቸው። ልብ ይበሉ በሀገር ቤት ያለው ወገንዎ ወይም ቤተሰብዎ በየቀኑ ይገደላል፣ በየእስር ቤቱ ይታጎራል፣ በየማጎሪያ ቤቶቹ ጆሮ ለመስማት የሚከብደው ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል፣ ዛሬም ግብር በሚባል የወያኔ የዘረፋ ዘመቻ የህዝባችን በገዛ ሀገሩ የመኖር ህልውና ገደል አፋፍ ላይ ደርሷል፣ በወያኔ የመሬት ዘረፋ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው አንሶ ለእስርና ለግድያ የተዳረጉ ወገኖች ጉዳይ በአለም ዐቀፍ ደረጃ ፊልም የሚሰራበት አሳዛኝ ታሪክ እስከመሆን ደርሷል።

ታዲያ እርስዎ ለዚህ ሁሉ የወገንዎችዎ ስቃይ ሲሉ የገዛ ገንዘብዎን ለወያኔ አልሰጥም ማለት ያቅትዎታል?

አዎ ለወገንዎና ቤተሰብዎ አብሮነት ሲሉ ገንዘቤን ለወያኔ አልሰጥም በሉ!!