በፈንሳይ በተከሰተው የሰደድ እሳት 10, 000 ሰዎች በአፋጣኝ ቦታውን እንዲለቁ ተደረገ

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

በፈረንሳይ በተከሰተው የሰደደ እሳት 4, 000 ሄክታር መሬት ላይ ከፍተኛ አደጋ እንዳስከተለ ተገለጸ።

ይህንን የሰደድ እሳት ለመቆጣጠር የፈረንሳይ መንግስት አጎራባች የሆኑትን የአውሮፓ ህብረት አገራትን እርዳታም መጠየቁም ታውቋል።

ወደ 10 000 የሚቆጠሩ የአባቢው ነዋሪዎች የሰደድ እሳቱ መስፋፋቱን ተከትሎ ቦታውን በፍጥነት ለቀው እንዲሄዱ ተጠይቀዋል።

ከሰኞ እለት ጀምሮ ከ 4, 000 በላይ የእሳት መከላከያ ብርጌድ አባላት ይህንን የሰደድ እሳት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ሪፓርቶች ያሳያሉ።

ከነዚህ የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ አባላት ውስጥ በትንሹ 12 በሰደደ እሳቱ ጉዳት ሲደርስባቸው ወደ 15 የፓሊስ አባላት የሰደድ እሳቱ በፈጠረው ጭስ መጠቃታቸው ተዘግቧል።

Saint-Tropez በመባል የሚታወቀውና በጎብኝዎች የሚመረጠው የመዝናኛ ሪዞርት በዚህ የሰደድ እሳት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበትም ተጠቅሷል።