አቡነ ጴጥሮስ ሰማዓት የሆኑበትን 81ኛ አመት መታሰቢያ በአል አታከብሩም ተብለን ተባረርን ሲሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ተናገሩ

0

የዛሬ 81 አመት በፋሽት ኢጣሊያ ስለሀገራቸዉ መስእዋት የሆኑትን የአቡነ ጴጥሮስን ዉለታ ለማስታወስ እና ለመዘከር ሀዉልታቸዉ ወደሚገኝበት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ነዋሪዎች ቢያመሩም በፀጥታ ሀይሎች መባረራቸዉን ገልፀዋል፡፡

ወጣቶቹ ጀግኖቻችንን ማሰብ ለምን እንከለከላለን? ብለዉ ቢጠይቁም ከፖሊሶች የተሰጣቸዉ ምላሽ ከበላይ አካል የተላለፈ መመሪያ መሆኑን ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል።

በስፍራዉ ወደ 3 መቶ የሚጠጋ ህዝብ ይጥል የነበረዉን ሀይለኛ ዝናብ ተቋቁሞ ለረጅም ሰአታት እንዲፈቀድለት ሲጠይቁ  የነበረ ቢሆንም  በአካባቢዉም ሆነ ከመታሰቢያ ሀዉልቱ ጋር ፎቶ  ሲነሱ የነበሩ ግለሰቦችም ጭምር ፖሊሶች ሲከለክሉ እንደነበርም ታዉቋል።  መረጃዉን የሰጡን ወገኖች የአቡነ ጴጥሮስን መታሰቢያ በአል ለማሰብ ከአብያተ ክርስቲያናት የተገኘ አካል ባለማያታቸዉ የተሰማቸዉን ከፍተኛ ሀዘን ገልፀዋል።