የአሜሪካ ሳይንቲስቶች የሰውን ጽንስ ተፈጥሮ መለወጥ እንደቻሉ ተነገረ

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

የአሜሪካ ሳይቲስቶች የሰውን ጽንስ ተፈጥሮ መለወጥ እንደቻሉ በዚህም ከውልደት ጀምሮ የሚይዝን በሽታ እንዳይከሰት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የነበሩ በሽታዎችን በግኝቱ በመጠቀም ማስቀረት እንደቻሉ የሮይተርስን ምንጭ ጠቅሶ የዘገበው የቪ.ኦ.ኤ ዘገባ ይገልጿል።

የተፈጥሮ መጽሄት በተሰኘው ስይንሳዊ ዜና አብሳሪ መጽሄት ( the journal Nature) ላይ ታትሞ የወጣውን ግኝት ያረጋገጠው የኦሬጎን የጤናና የሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን Oregon Health and Science University (OHSU) በጥናቱ ሂደትም እስከዛሬ ድረስ በቻይና ተሞክረው እንደሚያውቁ ጠቅሶ ውጤቱንም አጥጋቢ እና አጥጋቢ ያልሆኑ እንደነበረ ያስረዳል።

ክሪስፕር ኬስ ዘጠኝ ልክ እንደ መቀስ አጉል የሆነውን ተፈጥሮአዊ ማህተም ያለበትን ክፍል ከማህተሙ በማላቀቅ የተረፈው ከህመም የጸዳው ክፍል ይባዛና ሽሉ አድጎ ጽንሱ ጊዜው ሲደርስ ጤናማ ሆኖ ይወለዳል ይላሉ።

ዋናው ስይንቲስት ሁዋን ካርሎስ ኢስፒዙዋ “የሰው ጽንስ ላይ ያለ ችግርን ጉዳት በማያመጣ መንገድ ለማረም እንደሚቻል አሳይተናል” በማለት ስለግኝታቸው አስረድተዋል።

በሰው ሰራሽ ማዳቀያ ዘዴ የታረመውን የተፈጥሮ ጉድለት እንዳለበት ከሚታወቀው አባለዘር ጋር በማዳቀል በርግጥ አራሚው እንደሚሰራ ማረጋገጥ ተችሏል በማለት ጽንሱ የተበላሸውን ትቶ የታረመውን ማህተም በመጠቀም እድገቱን እንደሚቀጥል ማሳየት ተችሏል ይላሉ።

ብዙ ዓለም አቀፍ ድረጅቶች ሳይንስ በዚህ በኩል ያደረገውን ግስጋሴ ይፈራሉ፤ ይቃወማሉ። በሌላ በኩል ህክምናን ለማሻሻል የሚደረገው ለዚህ የረቀቀ ጥናት የሚደረገውን መንግስታዊ ድጋፍ አይቃወሙም።

“እንዲህ ያለው ጥናት የሚረዳው ህጻናት በማህጸን እያሉ ወይም ልክ እንደተወለዱ የሚታይን ጉድለት ማረም ወይም ከህመምና ስቃይ ማዳን ነው” በማለት ሁዋን ካርሎስ ኢስፒዙዋ ተናግረዋል።