የደቡብ አፍሪካው ታቦ እምቤኪ እና የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኬንያውያንን ስለ ምርጫው ውጤት ችግር ተማጠኑ

0

አባይ ሚድያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

የደቡብ አፍሪካው ታቦ እምቤኪ እና የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኬንያውያንን ወደ አደባባይ ወጥተው ተቋውሟቸውን እንዳይገልጹ መማጠናቸውን ብሉምበርግ የዜና ወኪል ዘገበ።

የኬንያ ተቃዋሚ ክፍል ምርጫውን የሚቆጣጠረው የኮምፑዩተር ስረዓት ሰርሳሪዎች ገብተው ተንኮል ሰርተዋል በማለት የኬኒያ ተቃዋሚ ፓርቲ እየከሰሰ ይገኛል።

የዚሁ የኮምፑዩተሩ ስርዓት የበላይ ጠባቂ የነበረ ሰው ደግሞ ከምርጫው በፊት ተገድሎ መገኘቱ ይህን ጥረጣሬን እንዲገን አድርጎታል።

ኬኒያውያን ከተቋውሞ ሰልፍ ይልቅ በፍትህ ሂደት ቅሬታቸውን ማቅረብ አለባቸው በማለት ታቦ እምቤኪ እና ጆን ኬሪ አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። “መንገድ ላይ መውጣቱ አይበጅም” በማለት ኬሪ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ ተናግረዋል።

“ውሸት” ሰርሳሪዎች ኮምፒዩተሩን ሃክ በማድረግ የምርጫ ውጤቱን ለማጭበርበር ችለዋል በማለት የተቃዋሚ ፓሪቲው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

አስመራጭ ቦርዱም ይህን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ክስ ቢያጣጥለውም እሳቸው ግን ወንጀል ተሰርቷል በሚለው አቋማቸው ጸንተዋል።

በ2007 እኤአ እንደዚሁ አይነት ተመሳሳይ እሰጥ አገባ  ተከስቶ ወደ 1100 የሚጠጉ ሰዎች በተፈጠረው የእርስ በእርስ ግጭት ህይወታቸውን ሊያጡ እንደቻሉ ይታወሳል።

የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የዘንድሮው የኬንያ ምርጫ ስርአት ግልጽ ድምጽ ቆጠራው ታማኝ እና የምርጫ ቦርዱም ስራውን በአግባቡ መወጣቱን መስክረዋል።

ፍራንስ 24 የዜና ወኪልም የአውሮጳው ህብረት የምርጫ ታዛቢ በኬኒያ የተደረገው የምርጫ ሂደት መጭበርበር ያልታየበት በማለት ምስክርነቱን እንደሰጠ ዘግቧል።