የአባይ ግድብ ግንባታ ከ70% ወደ 60% ማደጉ (ማሽቆልቆሉ) አነጋጋሪ ሆኗል

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

በአፍሪካ ትልቁ ተብሎ የሚጠበቀው የአባይ ግድብ አምና ሜይ 28 ቀን 2016 (ግንቦት 20, 2008)፣ በወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ በተናገሩት መሰረት የሕዳሴ ግድብ 70% አልቆ ነበረ።

ከትናንት ወዲያ 8 ኦገስት 2017 (ነሐሴ 2, 2009) የመንግስት ቃል አቀባይ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል እንደገለጹት አሁን 60% የሚሆነው የግድቡ ስራ ተጠናቋል ብለዋል።

ግድቡ 2011 ላይ 80 ቢሊዮን ብር ወይንም 4.7 ሚሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎ የተጀመረ መሆኑ ይታወሳል። ይሁንና በተለያየ ወቅት ከመንግስት ቢሮ የሚወጡ አሃዞች ህዝብን እያወዛገበ እንደሚገኝ ታውቋል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በእርግጥ የህዳሴው ግድብ 20% የሚሆን ተሰርቷል ወይ ሲሉ ይጠይቃሉ።
ለተጨማሪ መረጃ ከስር ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ
http://www.sudantribune.com/spip.php?article59119
http://news.xinhuanet.com/english/2017-08/08/c_136506781.htm