በሻርለትስቪል ቬርጂኒያ ኩ ክለክስ ክላን የተሰኙት ነጭ ዘረኞች እና ተቃዋሚዎቻቸው ተጋጩ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

አጃን ፍራስ ፕሬስ እንደዘገበው ዛሬ ሻርለትስቪል ቬርጂኒያ በኩ ክለክስ ክላን የተሰኙት ነጭ ዘረኞች እና ተቃዋሚዎቻቸው መካከል ግጭት ተፈጥሯል። በቨርጂያ ግዛትም ጊዜዊ አዋጅ ታውጇል። ፖሊስም ትይንተ ሃዝቡ እንዲበተን አድርጓል።

ኩ ክለክስ ክላን ጋር ዘመናይ ናዚዎችም ተጨምረዋል።

በቨርጂኒያ ግዛት ብረት መታጠቅ የዜግነት መብት ነው። በዚህም ሰልፈኛው ብረት ቢጠቅምስ የሚል ነው የፖሊስ ስጋት።

የዘረኛው በኩ ክለክስ ክላን  አባላት ለሰልፉ ሲመጡ የወታደር ልብስ ለብሰው ነበር። ብረትም ታጥቀው ነበር ታውቋል።

ቴሪ ማኩሊፍ የቨርጂኒያው ገዢ ሰልፈኞቹ በሰላም ሃስባቸው ቢገልጹ ችገር አልነበርው ብለዋል። ሁኔታው አስገድዷቸው ግን ቀትር ላይ አስቸኳይ አዋጅ አውጀዋል።

ብዙዎችን ያስገረመው እንዲህ ያሉ የጥላቻ ድርጅቶች መልሰው አብበው ዛሬ መገኘታቸው ነው። ሆኖም በሰልፉ በብዛት የወጡት ዘረኞቹን የሚቃወሙ ነበር ይላል የፈረንሳዩ ይዜና ወኪል።

ሻርለትስቪል ቬርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂያ የተሰኝው በግዛቱ እውቅ የተምህርት ተቋም ያለበት ከተማ ነው።