አምሳ ዓመታት የምራብ አፍሪካዋን ቶጎን የገዛው መንግስት ህዝባዊ አመጽ እያናጋው ነው

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ሬውተርስ ዛሬ እንደዘገበው በቶጎ ህዝባዊ አመጽ ተነስቷል። ሁለት ሰዎች ሞተዋል። 13 ደግሞ ቆስለዋል። የሞቱትን ቁጥር 7 የሚያደርሱትም ዘገባዎች አሉ።

ህዝብ የሚጠይቀው የስልጣን ዘመን የተወሰነ ይሁን፤ ይከበርን ነው።

ፕሬዚዳንት ፋኡሬ ናሲምቤ እያዴማ አባቱ ቶጎን ለ38 ዓማታት ከገዛ በኋላ እሱ ደግሞ በ2005 ጀምሮ ተተክቷል።

ሰላማዊ ሰልፋኛው የተቃዋሚ ፓርቱውን ቀይ ቀለም ለብሶ ነው የወጣው። “50 አመታት ሲበዛ ነው” እያለ ዋና ከተማዋ ሎሜን አጥለቅልቋታል። በ1992 በህገ መንግስት የጸደቀውው የስልጣን ዘመን ርዝመት ይከበር ብሎ እየጠየቀ ነው። ፖሊስ ሰልፈኛው ላይ አስለቃሽ ጢስ ተኩሷል።

ሶኮዴ በተሰኘች ከሎሜ 338 ኪሎ ሜትር በምትገኝ ከተማ ፖሊስ የጥይት ተኩስ ከፍቷል። ከአገሩ መከላከያ ሚኒስትር የወጣው መግለጫ 12 ፖሊሶች ቆስለዋል ብሏል።

በ1992 ህገ መንግስቱ የስልጣን ዘመንን ቢደነግግም ፓርላማው ህገ መንግስታዊ ለውጥ እያጸደቀ እያዴማ ደጋግሞ ለምርጫ እንዲቀርብ አመቻችቷል።

በ2005 ፋኡሬ ናሲምቤ ለስልጣን በበቃበት ምርጫ ተቃውሞ ተነስቶ 500 ሰዎች ለሞት ተዳርገው ነበር።

የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ቲክፒ አትቻዳም “የመሰብሰብ ነጥጻነት ተነፍጎ እንዳሻው ልሁን የሚልን አገዛዝ እየተቃወምን ነው” ብሏል።