የኢትዮጵያ 11% ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዴት ለዜጎች የሞት መንገድ ሊሆን ቻለ? [በወንድወሰን ተክሉ]

0

[በወንድወሰን ተክሉ]

በኬኒያ ኢንደስትሪያል እስር ቤት በብሎክ ጄ እና በብሎክ ኤል [Block J & L]በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ጎብኝቼ ነበር። የኢትዮጵያዊያኑ እስረኞች ቁጥር ወጥ የሆነ አይደለም። እንደ ለዋጋ ንረት የተጋለጠ እቃ [Volatile market ]ዋጋ ከፍ ዝቅ እንደሚል [Fluctuate ]እንደሚያደርግ እጅግ ሲጨምርና እጅግ ሲያንስ ይታያል።

ሁሉም ወጣቶች ናቸው።ከ18-32ዓመት ባለው የእድሜ እርከን ላይ ያሉ ታናናሾቼ ቢሆንም እኔ ታናሻቸው እነዚህ ወጣቶች ደግሞ ታላላቆቼ የሚመስሉ ጉስቁልና ወጣትነታቸውን ለግዜው ቀምቶ ያለእድሜ የእርጅና እድሜ ገጽታን
ያላበሳቸው ናቸው።

“ጋሽዪ አሁን እኛ ደህና ነን።ከተቻሎት ለወንድሞቻችን ደቡብ አፍሪካ ላሉት ይደውሉልን” እያሉ ሲማጸኑ በእርግጥም ያለፉበትን እና የነበሩበትን የቤት ውስጥ እስር ጋር በማነጻጸር ዛሬ ያሉበትን የእስር ሁኔታን መግለጸቻው እንደሆነ እረዳለሁ።

ከሀገራቸው ከወጡ መጪው ጥቅምት ላይ ዓመታቸው ነው። እንደ ሰርዲን እቃ እና የእርድ ፍየየል በሽፍን የእቃ መጫኛ መኪና ተጭነው ወደ ናይሮቢና ሞምባሳ ከዚያም ወደ ታንዛኒያ በሚወሰዱበት ወቅት ቭይ ላይ ተያዙ። ያለዶክመንት ህገወጥ ሆኖ በመንቀሳቀስ ክስ ሶስት ወር ፍርድ ወይም 40.000 [400$] ቅጣት ተቀጥተው ወደ ሀገራቸው ዲፖርት እንዲደረጉ ይፈረድባቸዋል።

በቭይ ያለው እስር አስከፊ ነበር። ከዓመታት በፊት 140 ኢትዮጵያዊያን ተያዙ የሚለውን ዜና ኔሽን ላይ አንብቤ ሄጄ ባየሃቸው ግዜ የእስር ቤቱን አስከፊነት በወገኖቼ ላይ ዓይቼዋለሁ።
ሶስቱን ወር ጨርሰው ዲፖርት ሊደረጉ ሲሉ [የአሁኑቾ እዚህ ናይሮቢ እስር ቤት ያሉት ማለቴ ነው]አሻጋሪያቸው [Brokers]ከፖሊስ ጋር ይሻረክና ወደ ናይሮቢው ኢንደስትሪያል እስር ቤት [Industrial Remand]እንዲዛወሩ ያደርጋል። ምክንያቱም ወደ ሀገር ቤት ዲፖርት ተደርገው የግንኙነት ስራውን በውደቀቱ እንዲበጣጥሱበት አይፈልግምና።

በኬኒያ ስልጣን ያለው የፖለቲካ ስልጣን ሳይሆን የገንዘብ ስልጣን ነው።በኬኒያ ቁስ አካልን ብቻ አይገዛም።[በእርግጥ በመላው ዓለም የገንዘብ ሃያልነት ገኖ የወጣ ቢሆንም-ከኢትዮጵያ ጋር ስናነጻጽረው በኢትዮጵያ ስልጣን የገንዘብ ምንጭ ሲሆንና በሁሉ ነገር ላይ የማዘዝ ሃይል ሲኖረው በኬኒያ ግን ገንዘብ ነው የስልጣን ምንጭ እናም በሁሉም ነገር ላይ የማዘዝ ስልጣን ያለው ለማለት ነው]

ሁሉንም ይገዛልና ደላሎች እጅግ ከባድ ሚና ይጫወታሉ።በተለይ ደህና ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ ደላሎች ያሻቸውን የማሳሰር፣ዲፖርት የማስደረግና ዲፖርት ይደረጉ የተባሉትንም የማሳገድን መስል ሚና ሲጫወቱ ይታያል። እናም ወደ ሀገራቸው ዲፖርት መደረግ አልቻሉም፣ወይም ተለቀው ወደ “ተስፋይቱ “ሀገራቸው ደቡብ አፍሪካ ሲሞክሩ ዓይታይም። በቃ ቁጭ ብለው በእስር ቤት [መያዣ ሆነው ማለት ይቻለኛል]በእስር ቤት መጠበቅ ብቻ ነው ያላቸው እድል።

ከሁለት ዓመት በፊት በተመሳሳይ የመጋጋዣ መንገድ በሽፍን ኮንቴይነር የእቃ መኪና ሲጋዙ 56 ኢትዮጵያዊያን በዳሬሰላም ላይ ሞተው እንደተገኙ በወቅቱ ጽፌ ነበር።በዚህ ዓመት ሰኔ ወር በኮንጎ በተመሳሳይ መጋጋዣ ሲጋዙ የሞቶቱን በርካታ ኢትዮጵያዊያንን አስከሬንን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዞ ድርጅት [IOM]ያፋ አድርጋል።

በኢትዮጵያና ኬኒያ የጋራ ስምምነት ህግ መሰረት የሁለቱም ዜጎች ወደ ሁለቱም ሀገር ያለ ቪዛ እንደሚገቡ ቢፈቅድም ሞያሌ ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ እስከ 10ሺህ ብር በመክፈል ወደ ኬኒያ እንደሚገባ ከበቂ በላይ ማስረጃዎች አለኝ።ክፍያውን ያናሩት የሁለት ሀገር ብሮከሮች [Cartel ]እንደሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በዚህ ሁሉ ስቃይ የተሞላበት ጉዞ ዛሬም ጭምር በሞያሌ፣ማንዴራና መሰል ቦርደር ከተሞች ወደ ኬኒያ የሚፈልሰው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አይታይም።

አዲስ አበባ ላይ በምንሊክ ቤተ መንግስት የተቀመጠው ገዢው የህወሃት ስርዓት ኢትዮጵያ ከ2005 በተለይም ከ2006 ጀምሮ ሀገሪታ ከ11%- 12.4% ኢኮኖሚያዊ እድገት እያስመዘገበች ያለች መሆናን በመግለጽ ይታወቃል። ሜጋ ሜጋ ፕሮጄክቶችን እና ሰፊ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን እየገነባ እንዳለ ይገልጻል። ሁሉንም ማጣጣል ባይቻልም የቁጥሩን ተጋናኝነት በመግለጽ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን እና የተስፋፋውን መሰረተ ልማት እውነት ብለን በመቀበል የአንድ ድፍን ደርዘን ዓመት ድርብ አሃዝ እድገት ውጤቱ ምንድነው ብለን ግን እንድንጠይቅ ያስገድደናል።

**ከ11% የኢኮኖሚ እድገት ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እሚሰደዱት?

“ሀገሪታ ተለውጣለች-አድጋ ተመንድጋልች-ገንዘብ ከየት እንደሚመጣ ላላውቅ እችላለሁ ግን ገንዘብን በገፍ-በበርሜል የሚያንቅሳቅሱ ዓይቻለሁ” ያለኝ አንድ ከዱባይ-ታይላንድ ሲነግድ የነበረና በሃላም ከስሮ በመሰደድ በናይሮቢ እንጀራ ጋገራ ስራ ላይ የተሰማራ አዲስ ገብ ሰው ነው። ሀገሪታ ካደገችና ከተመነደገች ታዲያ ለምን ለመሰደድ በቃ በማለት ትጠይቁ ይሆናል።

“በአስርና ሃያ ሺህ ቀርቶ በመቶ ሺህ መንቀሳቀስ ይከብድሃል። የምትወዳደረው በአስሮች የሚቆጠር ሚሊዮን ከመደበው ጋር ነው።ያንን ሚሊዮን እንካን በየትም ብለህ ብታገኘው በእነሱ ስር ካልታቀፍክ በፍጹም መንቀሳቀስ አትችልም። ጠብቀው አፈር ድሜ ያበሉሃል” ይላል ።
ከእነሱ ጋር ካልሆንክ ሲል ከባለሃብቶቹ ጋር ማለቱ ሳይሆን ከስርዓቱ ማለቱ ነው።
`ሚስቱን ወደ ታይላንድ እሱ ደግሞ ወደ ዱባይ በመመላለስ ይነግድ የነበረው ይህ የትናትናው ነጋዴ የዛሬው እንጀራ ጋጋሪ [ከመጡ ዓመትም አልሞላቸውም] የትግሪኛ ቃንቃ ተናጋሪዎች እንዴት በእያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ጉምሩክ፣ኤርፖርት፣ፍቃድ እና ምዝገባ ክፍል ተቆጣጥረው ከእነሱ ብሄር ተወላጅ ውጪ የሆነን ነጋዴ አፈር እንደሚያስግጡ በምሬት ይናገራል።

በሚሊዮን የሚቆጠር ካፒታል ያለውን ንግዱን እስከመወረስ ያበቃውም ጉራጌነቱና ይግሬ አለመሆኑ እንደሆነ ይገልጻል።

ለመሆኑ ከሀገር የሚሰደዱትን ኢትዮጵያዊያንን ነገድ ልብ ብላችሁ ታውቃላችሁ?የደቡብ አፍሪካን ተጋዦችን በሞኖፖል ደረጃ ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች የተሰጠ ይመስል ከምባታው፣ሃዲያው፣ወላይታው ከ90%በላይ ሲይዝ ወደ የተ.መ.ድ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት [UNHCR]በመቅረብ ለዓለም አቀፉ የስደተኝነት እውቅና የሚመዘገበው ደግም ኦሮሞውና አማራው እንደቅደም ተከተላቸው አንደኛና ሁለተኛ ሲሆኑ ሶማሊዎች ቀጥሎ ያለውን ስፍራ ይይዛሉ።
ከ10ሺህ ስደተኛ ውስጥ በጣት የሚቆጠሩ ከ2-4 የትግራይ ተወላጆችን በመከራ ብታገኝም እነሱም ወይ የቀድሞ ስርዓት ሰራተኞች የነበሩ ወይም ታጋይ ሆነው በምግባረ ብልሹነት፣ወንጅል ያኔ በ1980ዎቹ ውስጥ ከድርጅቱ የተባረሩ ግን ዛሬም በስደትም ሆነው ለድርጅቱ [ህወሃት]ጥቅም ጥብቅና ቆመው የሚሞግቱ ሆነው እናገኛለን።
ኬኒያ ትንሻ የመሰደጃ በር ነች ማለት ይቻላል ከአጠቃላይ ተሰዳጁ ቁጥር አንጻር-መንግስት አልባዋ ሱማሊያ፣አንዳችም የስራ እድል የሌላት ጅቡቲ፣መረጋጋት የናፈቃት ደቡብ ሱዳን እና የህወሃት ሁለተኛ ቤት የሆነችው ሱዳን በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በየወሩ ይሰደዱባቸዋል።

አሻጋሪዎች በዚህ ስስ ብልት በመግባት ህይወታቸውን ለአደጋ በሚያጋልጥ መንገድ እየወሰዱ ህይወታቸውን ለባህር ገንዘባቸውን ደግሞ ወደ ኪሳቸው እያደረጉ የደም ሀብት ያከማቻሉ።በነሀሴ 8እና 9ቀን 2017 ከ300በላይ ስደተኞች በቀይ ባህር ላይ ተጥለዋል። ሱማሌዎች ቢኖሩበትም የሚበዙት ኢትዮጵያዊያን ናቸው።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደሚባለው አድጎ ሊሆን ይችላል።የእድገቱንም መገለጫዎች ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ሳይሆን የስርዓቱን አራማጆች ብቻ በሚያንቀባርር መልኩ የሚመራ በመሆኑ ለብዙዎች መፈናቀልና መሰደድ ምክንያት ለመሆን ችላል።

Total Submission ነው ከህዝቡ የሚፈልጉት ” ያለኝ የ30ዓመቱ የአሩሲ ተወላጅ መሀመድ ከዲር ሲሆን በሀገሩ በርእሰ መምህርነት ለ4ዓመታት ያገለገለ ሰው ነው። “አንተ ምናልባት ፖለቲካ የሚባል የማትፈልግ ልትሆን ትችላለህ።በቃ የተቃዋሚም ሆነ የገዢ ፓርቲ ደጋፊ ሳትሆን መኖር የምትፈልግ ባለሙያ፣ነጋዴ፣ምሁር..ወዘተ ልትሆን ትችላለህ።እናም አባልነቱን እንቢ ትላለህ በጸባይ።ኦሮሞ ከሆንክ ኦ.ነ.ግ ነህ ትባላለህ-አማራ፣ጉራጌ፣ሱማሌ ከሆንክ ደግም ግንቦት 7 እና ኦ.ብ.ነ.ግ ትባላለህ።በዛም አያቆሙም ቁም ስቅልህን ያሳያሁል። ህግና መመሪያ ተከትለህ በትክክል ብትሰራም አንተ ትክክል ዓይደለህም።እድገት ይታለፍሃል። ጥቅማጥቅም ትነፈጋለህ ስራህንም ይነጥቁህና ለእስር ወይም ለስደት ይዳርጉሃል” ይላል መሀመድ።

የፖለቲካው ምህዳር ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚውም እጅግ ጠባል።የራስህን ቤት ቀለም ለመቀባት እንካን አስፈቅደህ ነው ምክንያቱም ትግሬ አይደለህምና።ትግሬዎቹ ቀለም መቀባት ቀርቶ ቦታ ነጥቀውና ሰርቀው በጨለማ የሚሰሩት ቤት የጨረቃ ቤት ተብሎ አይፈርስባቸውም። ንብረታቸው በየኬላ የሚያዘውና የሚወረሰው የትግሬዎቹ ሳይሆን የኦሮሞው፣የጉራጌውና የአማራው ነው። እንዴት አድርገህ ነው በዚህ መሰል አስራርና ስርዓት ስር በሀገርህ የቻልከውን እየሰራህ መኖር የምትችለው ይላሉ አብዛኞቹ የቅርብ ዓመታት ስደተኞች እና ከሀገር ኮብላዮች።

የኢኮኖሚው ምህዳር መጠበብ እጅግ ጥቂት የሆኑ ቢሊየነሮችን ቢፈጥረም እጅግ በርካታ የሆኑትን ደግሞ ከፖለቲካዊው ምህዳር መጥበብ ይበልጥ በሀገራቸው እንዳይኖሩ በማድረግ ሲያሰደድ ይታያል።

“ኢኮኖሚያዊ የበላይነትን ሳትቀደጅ የፖለቲካ የበላይነትህን ማስጠበቅ አይቻልህም ” የሚለው የህዋታዊያኑ ፍልስፍና ኢትዮጵያዊያኑን ሀገርና ቤት አልባ ሲያደርግ ህዋታዊያኑን ግን የሀገር፣የስልጣን እና የሀብት ባለቤት እያደረጋቸው ነው።

ይህ እስከመቼ እንደሚቀጥል ግዜውን በመግለጽ ደረጃ አይቻለኝ ይሆናል፡ግን በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ይህ ሁኔታ ከቶም ቢሆን አይቀጥልም።
`በቃ-ምንም ቢያደረጉ -ይህ ሁኔታ አይቀጥልም።እንኩትኩቱ የሚወጣበትም ወቅት ማንኛችንም ከምንገምተው በላይ እጅግ ቅርብ ነው።