የላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው ግሩፕ አባላት ለአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች እርዳታ መለገሳቸው ታወቀ

0

አባይ ሚዲያ
ፀሎት ዓለማየሁ

በትላንትናው እለት ነሃሴ 14 ቀን 2009 ዓ.ም (ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው)  በሚል ስያሜ በአለም አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ ድረገጽ በመሰባሰብ ሃገራችንን ከገጠማት አስጊና አሳፋሪ የህልውና አደጋንን ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ኢትዮጲያዊያን  ለአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በግምት ከ35,000 ዶላር በላይ የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ እና ልዩ ልዩ መገልገያዎች እርዳታ መበርከቱ ታወቀ ።

በዚሁ የስጦታ ስነስርዓት ላይም የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር የሆኑት አርበኛ ታጋይ ነዓምን ዘለቀ በአካል የተገኙ ሲሆን  እንዲሁም የአርበኞች ግንቦት 7 ድጋፍ አስተባባሪዎች በተገኙበት የርክክብ ስነስርአቱ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ቨርጅንያ  ከተማ  መፈፀሙ ታውቋል።

(ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው) የአለም አቀፍ  ማህበር ተወካዮች፣ ስጦታውን ለአርበኞች ግንቦት 7 ተወካይ  ካስረከቡ በኋላ ለእቃው ማጓጓዣ የሚሆን 700 የአሜሪካ ዶላር በጥሬ ገንዘብ  ሰጥተዋል ።

በእርክክቡ ወቅትም የላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው ዋና አስተዳደር በቃል አቀባያቸው በኩል ከአውሮፓ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል።

(ላንቺ ነው ኢትዮጵያ) በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ አህጉር እና ሀገሮች በማህበራዊ ድረገፅ የተሰባሰብን ኢትዮጵያውያን ህዝባችንን ከወያኔ የጭካኔ አገዛዝ ለማላቀቅ የሚታገሉትን የነፃነት ኃይሎች በምንችለው ሁሉ በቀጣይነት ለመርዳት ቃል ገብተናል። አሁንም ይህንን ግምቱ 35,000 ዶላር  የሚሆን የመጀመሪያ እርዳታ ህክምና መስጫ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ስናበረክት በመላው የማህበራዊ ድረገፅ አባላት እና የክብር አባሎቻችን ስም የተሰማንን ልባዊ ደስታ እንገልፃለን ብለዋል። ወደፊትም ይበልጥ ተደራጅተን በመጠናከር ከህዝባችን ጎን ለመቆም በድጋሚ ቃል እንገባለን።

ከዚህም በላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህዝባችን ህልውና ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመከላከል እና ሀገራችንን ከመፍረስ ለመታደግ እንዲተባበር በዚህ አጋጣሚ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በተጨማሪ የእምነት አባቶች እና እናቶች፣ የእውቀት እና የእድሜ ባለፀጋዎች እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ አክቲቪስቶች እና የመገናኛ ብዙሃን ለሃገራችን ህዝብ አንድነት ጉልበት መፈጠር የበኩላቸውን ወሳኝ ድርሻ ለማበርከት ይተባበሩልን ዘንድ በአጽንዖት እንጠይቃለን።

ለህዝባችን የአንድነት ጉልበት መፈጠር የሚረዱ መድረኮችንም  አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉ ለማመቻቸት በማህበራችን ስም ከወዲሁ ቃል እንገባለን።

ፈጣሪ ሃገራችንን ከዚህ የህልውና አደጋ ይጠብቅልን።
አሜን።
ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የተሰባሰብነው!!!
የቡድኑ መሪ • ዲና ኦል

በማለት መልዕክታቸውን ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ አስተላፈዋል፡፡