ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
- ለኦሮሚያ ክልል ለ10,314,270 ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ 3,439 ቢሊዩን ብር ብድር ተመድቦል፣ የነፍስ ወከፍ ብድር ድርሻ 333 ብር ነው፡፡ የኦሮሚ ወጣቶች ለ5 ቀናት የሚቆይ ከቤት ያለመውጣትና ያለመገበያየት አድማን ሌሎቹም ክልሎች ይቀላቀሉ!!!
- ለአማራ ክልል 8,024,773 ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ 2,679 ቢሊዩን ብር ብድር ተመድቦል፣ የነፍስ ወከፍ ብድር ድርሻ 334 ብር ነው፡፡ የአማራ ወጣቶች ለ5 ቀናት የሚቆይ ከቤት ያለመውጣትና ያለመገበያየት አድማን ሌሎቹም ክልሎች ይቀላቀሉ!!!
- ለሰላሣ ሚሊዩን ወጣቶች አሥር ቢሊዩን ብር ብድር ማለት 334 ብር የነፍስ ወከፍ ብድር ድርሻ ነው፡፡ ከኢትዩጵያ ህዝብ 70 በመቶ ወጣቶች ስትሆኑ፣ መጪውን ህይወታችሁን ለማስተካከል የህወሓት ፋሽስታዊ ሥርዓት ለመገርሰስ ታገሉ፡፡
በሃረሪቱ በተቀሰቀሰ ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ ተጋድሎ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ውድ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩት ቆስለዋል በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ለወህኒ ቤቶች ተሰቃይተዋል፣ ሰማንያ ስምንት ሽህ ዜጎች ሃገር ጥለው ተሰደዋል፡፡ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ የነፃነት ታጋዩች፣ ጠመንጃ የታጠቁ፣ክላሸን ኮቨ ያነገቡ፣ መትረየስ የደገኑ፣ ላውንቸር የተሸከሙ፣የእጅ ቦንብ የታጠቁ፣ የወያኔን ቅጥረኛ ሠራዊትን እነ ዝናር በቅፊን ድባቅ እየመቱ እብስ ማለት ጀምረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ያስደነገጠው የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት በየክልሎቹ ወጣቶቹን እየሰበሰቡ የሥራ እድል ልንከፍትላችሁ ነው!!! ህይወታችሁን ሥርታችሁ ትቀይራላችሁ!!! ‹‹ፀረ ህዝብ›› ኃይሎችን አትቀላቀሉ!!! መንግሥት ለወጣቶች አሥር ቢሊዩን ብር የብድር በጀት በመመደብ ወጣቶቹን ለመደለል በመሞከር ላይ ናቸው፡፡
‹‹የመቋቋሚያ ፈንዱ ምንጭ የፌዴራል መንግሥት የሚመድበው አሥር ቢሊዩን ብር በጀት እንደሚሆን አዋጁ ያስረዳል፡፡ ፈንዱን የሚያስተዳድረው የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ እንደሆነ፤ነገር ግን የፈንዱ ተጠቃሚዎች አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ብድሩን የማቅረብ ሥራ እንዲሠሩ፤ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በሌሉበት ደግሞ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብድሩን እንዲያቀርቡ ተደንግጓል፡፡››
‹‹ በዚህም መሠረት የንግድ ባንክ ኃላፊነት ለክልሎች የተደለደለውን በመለየት ለሚመለከታቸው አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ማስተላለፍ፤ተቋማቱ የተላለፈውን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ ማዋላቸውን መቆጣጠር፤ ስለፈንዱ ገንዘብ አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሪፖርት በየስድስት ወሩና በዓመቱ የተመረመረ የፈንዱ ሒሳብን ለገንዘብና ለኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ማቅረብ ይገኙበታል፡፡››
‹‹የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይም እርሱ የሚመድበው ኦዲተር በየዓመቱ የፈንዱን ሒሳብ የመመርመር ኃላፊነት ተስጥቶታል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል ደግሞ የክልሉን ድርሻ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ትንበያዎችን መሠረት በማድረግ መደልደል፤ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመመካከር በፈንዱ ለሚሸፈኑ ፕሮጀክቶች የሚሰጥ የብድር ጣሪያ፤ የወለድ መጠን፤ የእፎይታ ጊዜና ተከትሎ የሚያልቅበትን ጊዜ የተመለከቱ መመርያዎችን የማውጣትና የመወሰን ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡››
‹‹ ከፈንዱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት ከ18 እሰከ 34 ዓመት የዕድሜ ክል ውስጥ የሚገኙ ማንኛውም ኢትዩጵያዊያን መሆናቸውን አዋጁ ያመላክታል፡፡ ከፈንዱ የክልሎች ድርሻንና ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቁ ወጣቶችን የሚመለከተውን ዝርዝር መረጃ በቀጣዩ ስንጠረዥ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡››
ከ18-34 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ወጣቶች ብዛት በክልሎችና በከተማ መስተዳደሮችችና
የፈንድ ገንዘብ (ብር 10 ቢሊዩን) ድርሻ
ተ/ቁ | ክልል/ከተማ | ከ18-34 ዕድሜ
ወጣት ብዛት |
ከጠቅላላ ወጣት
ያለው ድርሻ () |
ከብር 10 ቢሊዩን
ያለው ድርሻ |
(1) | (2) | (3) | (4= 3 x 10 ቢሊዩን | |
1 | አፋር | 618,827 | 2.06 | 206 |
2 | ትግራይ | 1,578,463 | 5.27 | 527 |
3 | አማራ | 8,024,773 | 26.79 | 2679 |
4 | የኢትዩጵያ ሶማሌ | 1,806,539 | 6.03 | 603 |
5 | ኦሮሚያ | 10,314,270 | 34.39 | 3439 |
6 | ቤኒሻንጉልጉሙዝ | 338,433 | 1.13 | 113 |
7 | ደቡብ | 5,643,731 | 18.82 | 1882 |
8 | ጋምቤላ | 150,414 | 0.50 | 50 |
9 | ሐረሪ | 80,259 | 0.27 | 27 |
10 | አዲስ አባባ | 1,255,486 | 4.19 | 419 |
11 | ድሬዳዋ | 164,762 | 0.55 | 55 |
ጠቅላላ ድምር | 29,975,958 | 100 | 10 ቢሊዩን |
ምንጭ፡- የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ
ከ18 እስከ 34 የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ 29,975,958 ሚሊዩን ወጣቶች አሥር ቢሊዩን ብር ብድር ማለት 334 ብር የነፍስ ወከፍ ብድር ድርሻ ማለት ትልቅ ቀልድ ነው እንካኳን ህይወታቸውን ሊለውጥ ቀርቶ አንድ ዶሮ አይገዛላቸውም፡፡
የኢትዩጵያ የቤት ሠራተኞች ዜጎች ስደት Migrant Domestic Workers
የሰራተኛና ማህበራዊ ኑሮ ጉዳይ ሚኒስቴር ( MoLSA Ministry of Labour and Social Affairs) በተገኘው መረጃ መሠረት በኢትዩጵያ በአምስት ክልሎች ወደ ውጭ አገራቶች የፈለሱ የቤት ሠራተኞች ብዛት በአራት ዓመት ከ8 ወራቶች ውስጥ ያለውን ህጋዊ የቤት ሠራተኞ ስደተኞችን በግል ሠራተኛ ቀጣሪ ኤጀንሲዎች( PEAs Private Employment Agencies) አመቻችነትና የሰራተኛና ማህበራዊ ኑሮ ጉዳይ ሚኒስቴር አፅዳቂነት የተላኩ ኢትዩጵያዊያን ናቸው፡፡
Table 1:- Number of migrant domestic workers from five regions for 4 years and 8 months time
Region | 2008 Sept.-
2009 August |
2009Sept.-
2010 August |
2010Sept.-
2011 August |
2011Sept.-
2012June |
2012 July-
2013 February |
Total |
Tigray | 949 | 573 | 1,582 | 8,592 | 4,966 | 16,662 |
Amhara | 3,551 | 1,952 | 10,769 | 62,836 | 33,831 | 112,939 |
Oromia | 3,600 | 2,757 | 10,430 | 64,431 | 39,185 | 120,403 |
SNNP | 1,981 | 1,300 | 4,547 | 23,392 | 13,813 | 45,033 |
Addis Ababa | 7,251 | 6,860 | 11,813 | 26,774 | 11,472 | 64,170 |
Total | 17,332 | 13,442 | 39,141 | 186,025 | 103,267 | 359,207 |
በግል ሠራተኛ ቀጣሪ ኤጀንሲዎች የሠራተኛ ቅጥር ፎርም በማስሞላት፣ከኤጀንሲው ጋር የሚላኩት የቤት ሠራተኞች በመፈራረም፣ የቤት ሠራተኞች ወጪ በመሸፈን፣የቪዛ አገልግሎት ለሚሄዱበት አገር በመክፈል፣ደርሶ መልስ የዓየር ትኬት በመቁረጥ፣የመኖሪያ ፍቃድና የሥራ ፍቃድ ክፍያና ዋስትና ሽፋን (ኢንሽራንስ)በመግባት የመሳሰሉት ወጪዎች በኤጀንሲው ይሸፈናሉ፡፡ ቀጥሎ ያለው ሠንጠረዥ ከኢትዩጵያ ወደ አረብ አገራቶች የፈለሱ የቤት ሠራተኞች ብዛት ያሳያል በዚህም መሰረት ሳውዲ አረቢያ 76 በመቶ እጁን ሥትይዝ በመቀጠል ኩዌት 24 በመቶ የቤት ሠራተኛ እንደቀጠሩ ማስረጃው ያሣያል፡፡
Table 2:- The number of migrant domestic workers to the Gulf from September 2008 to February 2013
Country | 2008 Sept.-
2009 August |
2009Sept.-
2010 August |
2010Sept.-
2011 August |
2011Sept.-
2012June |
2012July-
2013 February |
Total |
Saudi Arabia | 9,399 | 2,395 | 13,446 | 158,959 | 92,691 | 276890 |
Kuwait | 6,976 | 10,837 | 25,457 | 28,476 | 11,440 | 83186 |
Dubai | 113 | 142 | 510 | 321 | 0 | 1086 |
Others | 905 | 19 | 115 | 175 | 59 | 1273 |
Total | 17,393 | 13,393 | 39,528 | 187,931 | 104,190 | 362435 |
ኢትዩጵያ የሠራተኛ ስምምነት የፈረመችው ከኩዌት ጋር ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ሳውዲ አረቢያ በቀን 1500 የቤት ሠራተኞች በቀን የምትወስደው አገር የሠራተኛ ስምምነት ጥያቄን ውድቅ በማድረግ ለመፈረም አሻፈረኝ ብላ ቆይታለች፡፡ የዜጎች ሞት፣በአመዛኙ እራሳቸውን የማጥፋት ስበብ/ምክንያት፣የወሲብ ትንኮሳ፣ የሥነ-ልቦና ቀውስ፣ የአካል ጉዳት ስቃይ ለመከታተል፣ የኢንባሲዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድጋፍ ይጠይቃል፡፡
ኢትዩጵያ መንግስት ከሳውዲ ዓረብያ በግፍ የተባረሩ ከ150 ሽህ ዜጎች ሠራተናችና ስደተኞች እንደ አውሬ እየታደኑ መባረራቸው የቅርብ ግዜ ትዝታ ነበር፡፡ የህወሓት መንግሥት ከኩዌት፣ከኳታርና ከዩርዳኖስ መንግስታት ጋር የቤት ሠራተኞች ለመቅጠር የሁለትዮሽ የሥራ ሥምሪት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ለኢትዩጵያውያን ትልቅ ገበያ የሆኑትን ሳውዲ አረብያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አገራቶች የህወሓት መንግስት ሹማምንቶች በማማለልና በመደለል ላይ ይገኛሉ፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች ልጆቻቸውን ወደ ባህር ማዶ አገራቶች ዶላር ከፍለው እያስተማሩ ሌሎቹን የእንጀራ ልጆች አረብ አገራት በቤት ሠራተኝነት ስራ አሰማርተው እነሱ ወደሃገር ቤት ለዘመዶቻቸው የሚልኩትን ዶላር የሃገሪቱ ትልቁ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ፣ የኋላ ገቢ መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ ከውጪ የሚላክ ገንዘብ/ ኋላ ከሃገሪቱ ከምታገኘው የውጪ ንግድ መብለጡን ስንት ዲያስፖራ ያውቃል፡፡ ዲያስፖራው በእጁ ላይ ያለውን የገንዘብ መብት ቢጠቀም የህወሓት መንግስትን መቅጣት ይችል ነበር፡፡ በ2008 ዓ/ም በተነሳው ህዝባዊ እንቢተኛነትና ተጋድሎ የህወሓት መንግስት ከውድቀት ያገገመው ዲያስፖራው በላከው 4 ቢሊዩን ዶላር መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን!!! ለዚህ ነው የሃሪቱን ኢኮኖሚ የማያውቅ ፖለቲካውንም አያውቅም የሚባለው፡፡
የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ወደ ውጭ አገራቶች የቤት ሠራተኞች በብዛት በመላክ የውጪ ምንዛሪ ያግበሰብሳል፡፡ በኢትጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ሐዋላ ፍሰት ከመደበኛ (ህጋዊ) በሆነ መንገድ (መኒ ግርሃም፣ ዌስተርን ዩኒየን፣ድሃብሽን ወዘተ) እንዲሁም በአመዛኙ መደበኛ ባልሆነ (ህገወጥ) መንገድ የውጪ ምንዛሪ ውጭ ካሉ ዜጎቹ ይሰበስባል፡፡ ከ2008 እስከ 2013 እኤአ ከአረብ ሃገራት ከሚኖሩ 362435 የቤት ሠራተኞች፣ ኢትዬጵያዊያን ነዋሪዎች /ዲያስፖራ/ ሃገር ቤት ላሉ ቤተሰቦችና ዘመዶች በመኒ ግርሃም፣ ዌስተርን ዩኒየን፣ድሃብሽን ወዘተ የላኩት ዶላር በኢትዩጵያ ባንኮች ገቢ ሆኖ ባንኮቹ ለዘመዶቻቸው በብር ይሠጡላቸዋል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት የቤት ሠራተኞች ወደ አረብ አገራቶች በመላክ ሠራተኞቹ ለወላጆቻቸው ከውጭ የሚልኩት ዶላር (ሃዋላ) ትልቁ ገቢው ነው፡፡
አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ታህሥስ 17 ቀን 2009ዓ/ም ‹‹ምጣኔ ሃብት ሲያድግ ስደት ለምን?›› በሚል ርዕስ በኢትዩጵያ በዓመት ከአንድ ሽህ ዜጎች መካከል ዘጠኙ ወደ ሌሎች አገራት ይሰደዳሉ፡፡ በ2015እኤአ በኢትዩጵያ የሥነ–ህዝብ ቁጥር 99,465,819 ሚሊዩን ውስጥ 895,192 ሽህ ህዝብ በዓመት እንደሚሰደዱ ተገልፆል፡፡ በአይኦኤም መረጃ ሚያመለክተው ፣ በህጋዊና ህገወጥ መንገድ 8 ሽህ ህዝብ በየዓመቱ ይሰደዳል፡፡ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶክተር ወልዳይ አምሃ እራሳቸው በጀርመን ሃገር ተሰደው ለስደተኞች የሚሰጥ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ተቀብለው ወደ ሃገር ቤት የገቡ ምሁር ናቸው፡፡ አሁን በስርአቱ ተጠቃሚ ሆነው ፎቅ ገንብተው ሆቴል ቤት ከፍተዋል፡፡ የኢትጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበርን ለህወሓት መንግስት አጎብዳጅ እንዲሆን ያደረጉ ካድሬ ናቸው ስለስደት ጥናት የሚያደርጉት፡፡ በኢትጵያ ውስጥ በየዓመቱ ሁለት ሚሊዩን ታዳጊዎች ወደ ወጣት የዕድሜ ክልል ይገባሉ በዚህም የተነሳ 1.4 ሚሊዩን ወጣቶች አዲስ የስራ እድል ሊከፈትላቸው ይገባል ማለት ነው፡፡ ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አሳየች የምትባለው ሃገር የስደት ችግርን ለመፍታት አቅቶታል፡፡
- Population 99,465,819, and expected to be 120 million in 2030 (CIA Fact book, August 2015)
ከዓለም ባንክና ከኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር በመተባበር የተሰናዳው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት መሠረት ‹‹በፋይናንስ ረገድ በተለይ በባንክ አገልግሎት እንዲሁም በመድህን ሽፋን አኳያ በተደረገው ጥናት መሠረት በአገሪቱ መደበኛ የፋይናንስ ተቆማት ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች ብዛት 22 በመቶ ብቻ ናቸው፡፡ (ማለትም ከ100 ሚሊዩን ህዝብ ውስጥ 22 ሚሊዩን ህዝብ የባንክና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው፡፡) ይህም ሆኖ የመንግስት ባንኮችና አነስተኛ የገንዘብ አቅርቦት የሚሰጡ ሆነው ሲገኙ፤ለቁጠባም ትልቁን ድርሻ የሚይዙት እነዚሁ ድርጅቶች ሆነዋል፡፡ 32 በመቶ ግለሰቦችና 48 በመቶ ቤተሰቦች እንደየአቅማቸው የቁጠባ ልምድ እንዳላቸው ተመዝግቧል፡፡ ይሁንና በአገር አቀፍ ደረጃ 600 ብር ለመቆጠብ አቅም ያላቸው ሰዎች ብዛት ከ30 በመቶ ያልበለጠ ሆኗል፡፡ ››
- Reflecting the prevalence of poverty in the region, data suggest that not more than 20 percent of adult Africans have a bank account, compared to between 30 percent and 50 percent in other developing regions. This can be attributed in part to high fees, low bank branch penetration and the extensive documentation requirements for opening an account.
በኢትዬጵያ ከውጭ የተላከ ገንዘብ በ2008 ዓ/ም 4 ቢሊዩን ዶላር ተመዘገበ
በኦሮሚያና በአማራው ክልሎች በሌሎችም ክልሎች በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ከባህር ማዶ ሃገራት ከሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን ሰደተኛች በቤተሰቦቻቸውና በዜጎች ላይ ለደረሰ የህይወት መሰዋትነት፣ እስራት፣ስደትና ንብረት መውደም ያደረጉት ድጋፍ፣ ከውጭ የተላከ የገንዘብ 4 ቢሊዩን ዶላር መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ ይህም የውጭ ሃዋላ አገሪቱ ከውጪ ንግድ ካገኘችው 2.86 ሚሊዩን ዶላር 71.5 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተስተውሏል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት በኢኮኖሚ እንዲያንሰራራና በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲጠናከር አድርጎታል፡፡ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን ይሄን የመንግስት የገቢ ምንጭ እስካላደረቁ ድረስና በሌላ መንገድ ገንዘብ መላክ ዘዴ እስካልተጠቀሙ ድረስ ህዝባዊውን ትግል መታፈኑ አይቀሬ ሆኖል፡፡ ስለዚህ የውጭ ሃዋላ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ተለያዩ ዘዴዎችን በመፍጠር የሙሰኛን መንግስትን የውጪ ምንዛሪ ገቢ ለማስቀረት መምከርና ዘዴዎች በመፍጠር ወገኖቻቸውን መርዳት ይጠበቅባቸዋል እንላለን፡፡
በአጠቃላይ ወጣቶች ለህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ተራ ፕሮፓጋንዳ ሳይወናበድ ህዝባዊውን እንቢተኛነትና ተጋድሎ በመቀጠል ነፃነቱን መቀዳጀት የግዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ የወያኔ ፋሽስታዊ ሥርዓት መውደቁ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ወያኔ በሙስናና በህዝብ ደም የተጨማለቀ የሽፍታ መንግሥት ነው፡፡ ወያኔ በመንግስት መዋቅር በመጠቀም፣ ኢፈርት፣ሜቴክ፣ሜድሮክ፣ ወዘተ በአዲስ አበባ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ የወያኔ ጀነራሎች፣ ባለሥልጣኖች፣ ዲፕሎማቶችና አባሪ የጊዜው ባለፀጎች በዘረፉት ገንዘብ ፎቅ በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ የህዝብ መሬት ነጥቆና ዘርፎ በጨረታ በመሸጥ በግፍ የተገነባ ሁሉ ነገ በህግ ፊት የህዝብ ሀብት መሆኑን መጠራጠር የለብንም!!! ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ ሸበጥ ተጫምቶና ቁምጣ ታጥቆ እንደመጣ ህዝብ ያውቃል ሌላ ምንም ንብረት አልነበራቸውም፡፡
ዛሬ ለነፃነትህ ዱር ቤቴ ብለህ የነፃነት ኃይሎችን የተቀላቀልክ ወጣት ነገ ሆ ብለህ በድል መግባትህን ለቅንጣት ያህል አትጠራጠር፡፡ ዝናብ ሲጥል ሲንጠባጠብ ፣ብሎም ሲያካፋ፣ ዶፉ ሲከተል፣ ከጠቡታ ውኃ ወደ ጎርፍ፣ ብሎም የወንዝ ሙላት፣ የምድር መጥለቅለቅ፣ የዓባይ ሙላት እንኳን ለሃገር ለኑብያና ምስር ይተርፍ አይደል፡፡ ለዚህ ነው ወጣት የነብር ጣት!!! አበው የሚሉት ዛሬ ትንሽ ሆኖ የተጀመረ ትግል ነገ እልፍ አዕላፍ እንሆናለንና በትግሉ እንፅና፡፡ ከነፃነት ምሽጋችሁ ሆናችሁ፣ ድቅድቁ ጨለማ ሲረታ፣ የጎህ ብርሓን ሲቀድ ከሩቅ ይታያልና!!!
የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!
ዶክተር መራራ ጉዲና፣ በቀለ ገርባ ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!
አንዳርጋቸው ጽጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!
አሳምነው ፅጌ፣ ተፈራ ማሞ፤ ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!
ክብር ለወደቁ የኢትዩጵያ አርበኞች!!!
ወጣት የነብር ጣት!!!