የአማራ ክልል በጎንደር የቅማንት ማንነት ላይ በመጪው ወር ሕዘበ ውሳኔ ለማካሄድ ወሰነ

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በአማራ ክልላዊ መስተዳድር በሰሜን ጎንደር 12 ቀበሌዎች ውስጥ ለሚኖሩ የቅማንትን የማነነት ጥያቄን ለመመለስ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በመጪው መስከረም ወር ውስጥ ህዝበ ውሳኔ/ሬፈረንደም እንዲያካሂድ መስማማቱን አስታወቀ።

ሆኖም ይህንን የክልሉን መንግስት ስምምነትም ሆነ የፌዴራል መንግስቱን የሬፈረንደም ውሳኔን የጎንደርን ሕዝብ ለመከፋፈልና ለማዳከም ታስቦ የሚሰራ የፖለቲካ ተግባር ነው ሲል ማውገዙ አይዘነጋም።

በሰሜን ጎንደር በመቶ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ የቅማንት ተወላጆች በፌዴራል መንግስቱ ጠያቂነት ከአማራ ጋር የሚለያቸውን የማንነት ጥያቄ አቅርበዋል በማለት የአማራ ክልላዊ መስተዳድር ልዩ ራስ-ገዝ ዞን እንዲፈቅዳላቸው በተሰጠ ትእዛዝ መስተዳድሩ ጉዳዩ ላይ ጥናት ካደረገ በኋላ ለ42 ቀን ቀበሌዎች ልዩ የአስተዳደር ዞንን ከሁለት ዓመት በፊት የፈቀደ ሲሆን ቆይቶም በፌዴራሉ መንግስት ግፊት 21 ቀበሌዎች በልዩ ዞን ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ በተቀሩት 12 ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩት ህዝቦች በማንነታቸው ላይ ህዝበ ውሳኔ መስጠት ይገባቸዋል በሚል የመስከረሙ ህዝበ ውሳኔ እንደተዘጋጀ ለመረዳት ተችሏል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባለሙያዎቹን ወደ ጎንደር ልኮ ቅድመ ጥናት ዝግጅት ማጠነቃቁን ገልጾ በተመደበለት የግዜ ገደብ ውስጥ ከአማራ ክልል መስተዳድር ጋር ሆኖ ህዝበ ውሳኔውን እንደሚያከናውን ገልጿል።