ዛሬ በይፋ የተጀመረው ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በሁሉም የኦሮሚያ ክልሎች አድማሱን እያስፋ ይገኛል

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በሁሉም የኦሮሚያ ክልሎች አድማሱን እያስፋ ይገኛል። ገና በማለዳ እንዳንድ ከተሞች በወስዱት እርምጃ ምክንያት ምንም አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት በከተማ ውስጥ አይታይም፤ ሻሸመኔ አውቶቡስ መናህሪያ ጸጥ ረጭ ብሏል። አምቦ ከተማ ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው።

በዚህ አድማ ማንኛውም ተሸከርካሪ በኦሮሚያ ጎዳናዎች ላይ አንደማይንቀሳቀስ እና አድማውን በመጣስ የስርዓቱ ተባባሪ በሚሆን በማንኛውም ተሸክርካሪ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ከዚህ ቀደም ማሳሳቢያ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ይሁን አንጂ ይህን ማሳሳቢያ በመተላለፍ በዛሬ እለት በሐመሬሳ ከተማ ሲንቀሳቀስ በነበረው ሰላም አውቶቢስ ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

አሁንም በቀጣይ ለ5 ቀናት በሚቆየው አድማ ማንኛውም የህዝብ ማጓጓዣ ተሸከርካሪ በኦሮሚያ ጎዳናዎች ላይ መንቀሳቀስ የማይችል መሆኑን እየገለጽን ይህን ማሳሰቢያ በመተላለፍ የገዢው እና የገዳያችን ተባባሪ በመሆን እንቅስቀሴ በሚያደርግ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ አንደሚወሰድ በድጋሚ እናሳስባለን፡፡

በኦሮሚያና አማራ ክልል የምትጓጓዙ ተሳፋሪዎች፣ በእናንተም ላይ መጉላላት እንዳይፈጠር ባትንቀሳቀሱ ተመራጭ ነው። በአዲስ አበባ፣ በላምበረት መናህሪያ አንዳንድ አሽከርካሪዎች አድማውን ለመቀላቀል እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ቃሊቲም ምልክት ይታያል ተብሏል።