የካናዳ መንግስት ትላንት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎቹ የጸጥታ ጉዳይ ያሰጋቸዋል የሚል ማስጠንቀቂያ አውጥቷል

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

የካናዳ መንግስት በኦፊሴላዊ ድረገጹ ባወጣው መግለጫ ወደ ሀረር፤ ድሬ ዳዋ፤ በሆለታ እና አምቦ መንገድ መካከልን በጸጥታ ችግር ምክንያት ይጠቅሳል። የስጋቱን ምክንያት እና አደጋው ዝርዝርን ግን አይገልጽም።

ካናዳ እንደሌሎች አገሮች ኢትዮጵያን በሙሉ የሚያጠቃልል የጉዞ ማስጠንቀቂያ ብታነሳም በተጠቀሱት ቦታዎች ዜጎቿ ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስባለች።

የአሜሪካን ኤምባሲ ባለፈው ሳምንት ከፍተኛ ውጊያ በሃረርና ባሌ መደረጉን ይፋ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል። የአዲስ አበባው መንግስት ግን ጉዳዩ እንደተለመደው አካክዷል ይላል ኦል አፍሪካ ንውስ የተሰኘ ጋዜጣ።