አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ በውጊያ ልምምድ ላይ እያሉ ሰሜን ኮሪያ ሶስት ሚሳይል ተኮሰች

0

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በአሜሪካን እና ሰሜን ኮሪያ መካከል በኒውክሌር እርሰበርስ መጠዛጠዝ ዛቻና ፉከራ በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ፒዮንግያንግ ሶስት መካከለኛ ርቅት ያላቸውን ሚሳይሎች ለሙከራ መተኮሷን የዛሬይቱ ሩሲያ [RT] የዜና ወኪል ገለጸ።

ፒዮንግያንግ ሶስቱን ሚሳይሎች በተኮሰችበት በዛሬው እለት በዋሽንግተን፣ ሶልና ወደ አስር የሚጠጉ ህብረት ሀገራት የተሳተፉበት ግዙፉ የተባለውን ወታደራዊ የጦር ልምምድ እያደረጉ ባለበት ወቅት ሲሆን ድርጊቱን ሰሜን ኮሪያ ለትንኮሳና ሉዓላዊነቴ ላይ ያነጣጠረ ስትል የምትገልጸው እንደሆነ ይታወቃል።

በሰሜን ኮሪያ ዛሬ ሶስት መካከለኛ ሚሳይሎች ወደ ጃፓን ውቂያኖስ የተተኮሱ ሲሆን ሁለቱ በጃፓን ውሃ ላይ እንደወደቀ ሲገለጽ አንደኛው ደግሞ ከተተኮሰ በኋላ በዓየር ላይ እንደፈነዳ ተገልጿል።

የፔንታጎን ባለስልጣናት የሚሳይሎቹን መተኮስ እውነት መሆኑን ለሪፖርተሮች ያረጋገጡላቸው ሲሆን የትራምፕ አስተዳደርም ሆነ የነጩ ቤት [ዋይት ሃውስ] በጉዳዩ ላይ እስከአሁን አስተያየት እንዳልሰጠበት ለማወቅ ተችሏል።

ባለፈው ሐምሌ ወር ፒዮንግያንግ አህጉር አቋራጭ [ከ10,000 ኪ.ሜ] በላይ የሚጓዝ ባሊስቲክስ ሚሳይል ለሙከራ ከተኮሰች በኋላ ግዛቱ በኢላማ ስር የወደቀበት የትራምፕ አስተዳደር ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ ለማድረስ መንቀሳቀስ ሲጀምር በኒውክሌር ደረጃ እርሰበርስ መዛዛትን ያስከተለን የቃላት ጦርነት መፍጠሩ ይታወቃል። ፕሬዚዳንት ትራምፕም በፒዮንግያንግ ላይ የከረርና ጠንከር ያለ ተጽእኖ ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ሰሜን ኮሪያ ከፒዮንግያንግ 34,000 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ያለውን የአሜሪካን የጦር ተቋም የመምታትን ውሳኔ በማራመድ ካስደነበረች በኋላ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ጆንግ አን ኢን በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ተኩስ የሚለውን ትእዛዛቸውን ለማጠፍ የቻሉ ሲሆን እርምጃውንም ዋሽንግተን በበጎ ዓይን በማየት አሞካሽተው እንደነበር አይዘነጋም።

የሰሜን ኮሪያ የአሜሪካንን የጦር ተቋም ለመሞታት ያሳለፈችውን ውሳኔዋን ማስተላለፍ ለዋሽንግተን እንደ ድል በመቁጠር ፒዮንግያንግ ከእንግዲህ ተማራለች ምንም ዓይነት የሚሳይል ሙከራዎችን የምታደርግ አይመስለንም በሚል ሙሉ እምነት በገለጹ ከ15 ቀን ባልሞላ ግዜ ውስጥ ያውም በቀጠናው ከፍተኛ የተባለለትን የወታደራዊ ጦር ልምምድ በሚያደርጉበት ወቅት የሰሜን ኮሪያን ሶስት ሚሳይሎች መተኮስ የአሜሪካንን ተስፋ ከንቱነትና ሰሜንን ያለማወቅ ያሳያል ሲሉ ተንታኞች ይናገራሉ።