የጊኒው የቀድሞ የማእድን ሚኒስትር በአሜሪካ 7 አመት ተፈረደበት

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ዋሽንተን ፖስት እንደዘገበው የጊኒው የቀድሞ የማእድን ሚኒስትር ያለፈው አርብ በአሜሪካ 7 አመት ኒው ዮርክ በዋለው ፍርድ ቤት ተፈርዶበታል። ሚኒስትሩ የተከሰሱት $8.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ በልተዋል በሚል ወንጀል ነው።

ፍርዱን የሰጡት ዳኛ የአሜሪካ ዜግነትን ይዞ እንዲህ አይነት ወንጀል መፈጥጸም አይቻልም ብለዋል። ሚኒስትሩም ጊኒን ከድተሃል ብለውታል።

የአሜሪካ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ ዴኒስ ኮቴ መሀሙድ ቲያም፣ ማለትም የቀድሞው ሚኒስትር፣ ወደ ጊኒ የሄደው “ሊረዳ እንጂ ሊዘርፍ አይደለም” በማለት ተናግረዋል። እንደደረሰ “በሙሰኞች ተከበበ፤ በመጨረሻም እራሱ ገባበት“ ሲሉ ዳኛይቱ ተናግረዋል።

የአሜሪካ የፌዴራል ህግ  ለእንደዚህ አይነቱ ወንጀል 12 ዓመት ብታች ይበይናል። የ50 አመቱ ወንጀለኛ በማጭበርበር እና ገንዘብ አለህግ በማዘዋወር ተይዞ ዘብጢያ የወረደው ካለፈው የፈረንጆች ወር ዲሴምበር አንስቶ ነው።

ወንጀሉ የተፈጸመው 2009 እና 2010 ዓ ም ነበር። ድርጊቱ ለአንድ የቻይና ትልቅ ኩባንያ ብቸኛ የንግድ መብትን ለመስጠት ጎቦ መቀብልን የተመለከተ ነው። የቀድሞ ሚኒስትሩ ወንጀሉን ክዶ እንዲያውም “ምን አጠፋሁና” የሚል እብሪትም ነበረው ብለዋል ዳኛዋ።

ሙስና ቻይና ባለበት፤ ኩበት ላም በዋለበት መገኘቱ አስያገርምም ይላሉ አፍሪካን በቻይና የሚከታተሉ።