ጥቁር አሜሪካዊው ሜይዌዘር ለ50ኛ ግዜ በማሸነፍ ሪኮርድ ሰበረ

አባይ ሚዲያ
በወንድወሰን ተክሉ

በታላቅ ጉጉት ተጠብቆ የነበረው በጥቁር አሜሪካዊው ሜይዌዘርና በአየርላንዳዊው ማክግሬገር መካከል የቦክስ ውድድር ዛሬ በላስቬጋስ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በአሜሪካዊው አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችላል።

የ28 ዓመቱ አየርላንዳዊ “This is my word , I will knock him out at 4th round” ያለውን ቃል መጠበቅ አቅቶት በ10ኛው ዙር ላይ እራሱ በዳኛ ጣልቃ ገብነት ቀሪዎቹን ሁለት ዙሮች መቀጠል አይችልም ተብሎ ለመሸነፍ እንደበቃ ከተላለፈው ሪፖርት መረዳት ተችሏል።

image

በዚህም ሜይዌዘር “I will knock him out, you line them up I will knock them one by one ” ያለውን ቃል ባስጠበቀ መልኩ በብዙዎቹ ፑንዲትስ ያሸንፋል የተባለውን አየርላንዳዊ በ10ኛው ዙር ላይ በበላይነት ለማሸነፍ መቻሉ ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

መቧቀሱ እንደተጀመረ ለሶስት ተከታታይ ዙሮች አየርላንዳዊው 9 ለ10 በሆነ ነጥብ እየመራ እንደነበረ ከዳኞቹ ሪፖርት ማወቅ የተቻለ ሲሆን ቀሪዎቹን ዙሮች እስከ አስር ድረስ ያሉትን ግን በሜይዌዘር 10 ለ9 መሪነት ሲቧቀሱ እንደነበር ያስረዳል።

በአስረኛው ዙር ላይ የሁለቱም አጠቃላይ ነጥብ የሜይዌዘር 87 እና ማክግሬገር 84 ነጥቦች በሆኑበት ደረጃ ሜይዌዘር ከግራና ከቀኝ በፍጥነት አከታትሎ ያቀመሰውን ቡጢ መቋቋም አቅቶት ለግልጽ መደብደብ ደረጃ ላይ የወደቀውን ማክግሬገር የዳኛው ጣልቃገብነት ተፈጥሮ ከባሰ ጉዳት በመዳን ውድድሩን ሜይዌዘር በማያወላዳ የበላይነት ቢያሸንፍም ተሸናፊው ግን ከውድድሩ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃል “ዳኞቹ እስከመጨረሻው እድል ሊሰጡኝ ይገባ ነበር ” ሲል ተደምጧል።

ሆኖም ሜይዌዘር በበኩሉ “ዛሬ ምሽት ጥሩ አስደናሽ አግኝቼያለሁ። ማክግሬገር ጥሩ ዳንሰኛና ጥሩ አስደናሽም ነው። እኔ በፊት ከገመትኩት ይበልጥ ጠንካራና ብርቱ ቦክሰኛ እንደሆነ አይቻለሁ። ሆኖም አሸናፊነቱን ያው ለአሸናፊው መተው አለበትና አሸንፌዋለሁ” በማለት የተጋጣሚውንም ጥንካሬና ብርታት ሳይሸሽግ ገልጿል።

image

በ40ኛ ዓመቱ ላይ ያለው ሜይዌዘር 50 ውድድሮችን ያለሽንፈት በመጨረስ ሪኮርድ ያስመዘገበ ብቸኛ ቦክስኛ በመሆን ጡረታ እንደወጣ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ በፊት 49-0 አሸናፊነትን ሪኮሪድ ከተጋራው ሌላ ቦክሰኛ በአንድ ድል በልጦ 50-0 ሪኮሪድ በማስመዝገብ ከቦክሱ እስፖርት በክብር ሊሰናበት የቻለ ድንቅ እስፖርተኛ ሆኖ የቦክስ ታሪኩን ደምድሟል።

በዛሬው ውድድር ከተገኘው 700 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ላይ 300 ሚሊዮን ዶላሩ ለሁለቱ ተቧቃሾች የተሰጠ ሲሆን ሜይዌዘር 70% ወደ ኪሱ መክተት እንደቻለ ተገልጿል።