የአገሬ ቀንደኛ ጠላት አይ ኤስ ነው በማለት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ተናገሩ

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ

የፈንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አገራቸው የእስልምና አክራሪ ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ ከሚጠራው አይ ኤስ ጋራ የሚደረገው ትግል ከምንም በላይ ተቀዳሚነት የሚሰጠው እንደሆነ አሳወቁ።

እራሱን አይ ኤስ ብሎ የሚጠራውን ድርጅት የፈረንሳይ ቀንደኛ ጠላት እንደሆነም ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናግረዋል።

ፈረንሳይ በተለያዩ ጌዜያት በደረሰባት ተደጋጋሚ የአይ ኤስ ጥቃት ከ240 በላይ ዜጎቿን እንዳጣች ሪፓርቶች ያመለክታሉ። ለ

አይ ኤስ መስፋፋት እንደ ዋና ምክንያት የሚጠቀሰውን የሶርያ ጉዳይን ለመፍታት አዲስና አለማቀፋዊ የሆነ አካሄድ ከሴፕተምበር ወር ጀምሮ ስራ ላይ እንደሚውልም ፕሬዝዳንቱ  ገልጸዋል።

የኢራቅና የሶርያ ሰላም መስፈንና መረጋጋት የፈረንሳይን ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር መታየት ያለበት ጉዳይ እንደሆነም አብራርተዋል።

የፈረንሳይ ጦር በከፍተኛ ደረጃ በአየርና በምድር ተሳትፎው የአይ ኤስ ሚሊሻዎችን በሶሪያና በኢራቅ እየተዋጋ እንደሆነ ይታወቃል።